Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከማይመቹ ሁኔታዎቼ

Kemayemechu Hunietawochie

2017 · ትራክ 11 · 4:42 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከማይመቹ ሁኔታዎቼ

ካልተመለሱ ጥያቄዎቼ

አንተን መጠጋት ተማርኩ ትዕግስትን

ያልክልኝ ብቻ ይሁን ማለትን (፪x)

እምነቴን ሊጨምር ሊያጠነክረኝ

በእርሱ መጓደዴን ከፍ ሊያደርግልኝ

ይበልጡን እንዳውቀው እርሱ ማን እንደሆነ

ብዙ ብዙ ነገር በህይወቴ ሆነ (፪x)

ለእራሴ ከማውቀው በላይ

እንደምታውቅልኝ አውቄያለሁ (፪x)

ፈጥነህ ብትመጣ ብትገኝ በቤቴ

መቼ ያልፍ ነበር ይህ ሁሉ በህይወቴ

እንዲህ ያለውን ስንፍና ከአፌ አላወጣም

ሟቹን ለማስነሳት እጆችህን አያጥሩም

ድንጋዩን አንከባለህ ግንዛቱን ፈተህ

ዳግም ማመላለስ ፍቃድህ ከሆነ

ሰው ሁሉ አልቅሶ ሲያበቃ ከጀመርክ

ይሁንልኝ እላለሁ ሁሉ እንደፈቃድህ

አይሆንም ስል ሆነ

አይነጋም ስልህ ነጋ

አልዘልቅም ስል ዘለቅኩ

በብዙ ጀገንኩኝ በእርሱ ስለተያዝኩ (፪x)

የትላንት ምሽቴ ምስጋናን : ወለደ

የዘገየው መልሴ በውበት ተገለጠ

የሌሊት ለቅሶዬ ሳቅን አመጣልኝ

ባንተ ጊዜ ሲሆን ነገሬ አጌጠልኝ

አይሆንም ስል ሆነ

አይነጋም ስልህ ነጋ

አልዘልቅም ስል ዘለቅኩ

በብዙ ጀገንኩኝ በእርሱ ስለተያዝኩ (፪x)

በብዙ በረታሁ በእርሱ ስለተያዝኩ

በብዙ ጀገንኩኝ በእርሱ ስለተያዝኩ

በብዙ በረታሁ በእርሱ ስለተያዝኩ

ከማይመቹ ሁኔታዎቼ

ካልተመለሱ ጥያቄዎቼ

አንተን መጠጋት ተማርኩ ትዕግስትን

ያልክልኝ ብቻ ይሁን ማለትን

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ