ጌታ ሆይ ተመስገን
Gieta Hoy Temesgen
2017 · ትራክ 9 · 6:27 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ ተመስገን ተመስገን ተመስገን
አድናቆት ያንስሃል ቢጨመር ቢጨመር ጌታ ሆይ ተመስገን
ጌታ ሆይ ተመስገን ተመስገን ተመስገን
ይሄ ሁሉ ያንስሃል ቢጨመር ቢጨመር ጌታ ሆይ ተመስገን
ቁጥር 1 · Verse 1
ለመንፈስ ድኅነቴ ምስራች የሰበከ
የልቤን መሰበር በቃሉ እውነት የጠገነ
ምርኮኛ የነበርኩትን ነጻነቴን ያወጀልኝ
በብዙ ለቅሶ ፈንታ መጽናናትን የላከልኝ
እጨምራለሁ ባያክልህ ባይመጥንም ጥግህም ባይደርስም
እጨምራለሁ ባያክልህ ባይመጥንም ጥግህም ባይደርስም
ለፍቅሬ መግለጫ ላድርግ የቻልኩትን
ጥሜን ባይቆርጥልኝ ባያረካም ውስጤን
ትናንትም ብያለሁ ዛሬም እደግመዋለሁ
መተኪያ የለህም እኔ እወድሃለሁ
አዝማች · Chorus
ተመስገን ፤ ተመስገን ፤ ተመስገን ፤ ተመስገን
ተመስገን ፤ ተመስገን ፤ ተመስገን ፤ ተመስገን
ሌላ የለኝም የሚጨመር ኢየሱሴ ተመስገን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ብዙ አድርገህልኛል ከቁጥር ያለፈ ከቃላት ያለፈ ከንግግር ያለፈ
ብዙ አድርገህልኛል ከቁጥር ያለፈ ከቃላት ያለፈ ከንግግር ያለፈ
የሕይወቴ ትርጉም ነህ የከፍታዬ ምክንያት
መዳን የሆንክላት ላንዷ ነፍሴ ወደህ የተቤዠሃት
ተስፋ የማደርግህ ትመጣለህ ብዬ
የእውነቱን ልናገር ከውስጥ ከመንፈሴ
ኑሮ መቃብር ነው ያላንተ ኢየሱሴ
የእውነቱን ልናገር ከውስጥ ከመንፈሴ
ኑሮ አይጥመኝም ያላንተ ኢየሱሴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ