ፈልጌህ
Yehonelegnal
2017 · ትራክ 3 · 6:27 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ይሆንልኛል ይሳካልኛል
ሥጋት ሰፈሬን ከራቀ ሰንበትበት ብሏል (፬x)
አልረሳውም ማንነቴን
በደም ዋጋ መገዛቴን
ንጉሥ ከላይ ሆኖ እንዳየኝ
ልጄ ምርጤ ርስቴ እንዳለኝ (፪x)
በምሰማው ሌላ ውሸት
አልጥለውም ይህን ዕውነት
ንጉሥ ልጁን የላከልኝ
የተወደድኩ ምርጥ ዘር ነኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
አይሆንም አይሰምርም ያለው ኧረ ማን ነው?
ሁኔታ ነው? ነቅቻለሁ!
ቃሉን በንጉሥ ቃል ሽራለሁ
ተደርጐልኛል ተሳክቶልኛል ይህን አውቃለሁ
አይሆንም አይሰምርም ያለው ኧረ ማን ነው?
ጠላቴ ነው? ነቅቻለሁ!
ቃሉን በንጉሥ ቃል ሽራለሁ
ይሆንልኛል ይሳካልኛል ይህን አውቃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ቁም ነገር አድርጐት የእኔን ጉዳይ
ክብሩን ሁሉ ትቶ ወርዷል ከላይ
አቅሜን አውቃለሁ በእርሱ ያለኝን
የሆንኩትን ሆኖ ያረገኝን (፪x)
ደዌ በእኔ ላይ ላይሰለጥን እርግማን በቤቴ እንዳይገኝ
ዝቅታ ላይሆንብኝ በላዬ መሸነፍ መረታት ላያገኘኝ
ከፍ ላለ ሕይወት በክርስቶስ ታጭቻለሁ ይህ ነው ዕጣ ፈንታዬ
የሆንኩትን ሁሉ ሆኖልኛል በድል ተፈጽሟል ጐዳናዬ
አዝማች · Chorus
ያለቀ ነው ያኔ ድሮ
የእኔ ጉዳይ የእኔ ኑሮ
በቀራኒዮ ተራራ ላይ
ተፈጽሟል ብሎኛል የእኔ ጉዳይ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ