ትልቅ የሆነውን
Teleq Yehonewen
2017 · ትራክ 1 · 4:28 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ትልቅ የሆነውን ከፊቴ አስቀድሜ
መቼ አንገቴን ደፋሁ መች ሄድኩ አቀርቅሬ
የተማመንኩበት ኩራቴ ሆኖኛል
ትላንቴ ይመስክር ሰልፌን አሸንፏል ፤ ሰልፌን አሸንፏል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከፍታውን ተመኝቶ ከፍ ብያለሁ ያለ
ላፍታ ማን ተመቸው ማን ተደላደለ
ወርዷል ወደ ቦታው እርሱ ወዳዘዘለት
ልክን ማወቅ እያለ ኋላ ከመዋረድ
በዕውቀቱ ልቀት ማንስ ገለጠው
እንኳንስ የእርሱን ጥግ ጫፉን ማን ነካው
ሁሉም ከታች ሆኖ ይመለከተዋል
የእጁ ስራ ሁሉ ሲያደንቀው ይኖራል
ከቶ አልደፍርም አንደኛ ልለው
ሁለተኛ ሆኖ ማን ተከተለው
ሁሌ ብቻውን ሚመለክ ትልቅ
ሚጨምር ክብር ከትላንቱ ይልቅ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ደጋግሞ ቢፎክር ቢጨምር ቀረርቶ
ልኩን አግብቶታል ከሰማያት ወርዶ
ዝቅ ብሎ ያለ ልክ ታዞ በመስቀል ላይ
የአብን ጥም አርክቷል ሆኗል የአለም ሲሳይ
ግድግዳው ፈረሰ በመሀከል ያለው
ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ለይቶ ያቆየው
ፍቅር መሀል ገብቶ ሁሉን : አንድ አረገ
ጠላትም አፈረ ለሁሌ እጁን ሰጠ
ከቶ አልደፍርም አንደኛ ልለው
ሁለተኛ ሆኖ ማን ተከተለው
ሁሌ ብቻውን ሚመለክ ትልቅ
ሚጨምር ክብር ከትላንቱ ይልቅ (፪x)
አዝማች · Chorus
ትልቅ የሆነውን ከፊቴ አስቀድሜ
መቼ አንገቴን ደፋሁ መች ሄድኩ አቀርቅሬ
የተማመንኩበት ኩራቴ ሆኖኛል
ትላንቴ ይመስክር ሰልፌን አሸንፏል ፤ ሰልፌን አሸንፏል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ