ጨለማዬ በራ
Chelemayie Bera
2012 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንቅፋት አይመታኝ ጉድጓድም አይጥለኝ
ጉድጓድም አይጥለኝ
አሃ እህ ጉድጓድም አይጥለኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
የህይወቴ ብርሃን ኢየሱስ አለለኝ አለልኝ
አልደናገርም በጉዞዬ ሁሉ በመንገዴ ሁሉ
አሃ እህ በመንገዴ ሁሉ
መንገዴን አነጻሁ በቅዱሱ ቃሉ ቃሉ ቃሉ 3
አዝማች · Chorus
በራ በራ በራ በራ በራ
ጨለማዬ በራ
በራ በራ በራ
ጨለማዬ በራ
ቁጥር 3 · Verse 3
ኑሮዬ ጨልሞ ጎጆዬም አዝምማ
ጎጆዬም አዝምማ
አሃ እህ ጎጆዬም አዝምማ
ቁጥር 4 · Verse 4
ጌታ ቤቴ ገባ ትንሣኤ ተሰማ ተሰማ
አሮጌውን ልብሴን አወለኩትና ወረወርኩትና
አሃ እህ ወዲያ ጣልኩትና
ጽድቁን አለበሰኝ በህይወት ልኖር ገና ገና ገና 3
አዝማች · Chorus
በራ በራ በራ በራ በራ
ጨለማዬ በራ
በራ በራ በራ
ጨለማዬ በራ
ቁጥር 5 · Verse 5
ባርነቴ አበቃ ከኃጢያት ገላገለኝ
ከኃጢያት ገላገለኝ
አሃ እህ ከኃጢያት ገላገለኝ
ቁጥር 6 · Verse 6
የውስጥ ዓይን በራ ከሰው ቀላቀለኝ ቀላቀለኝ
እመሰክራለሁ ያደረክልኝን የሰራህልኝን
አሃ እህ የሰራህልኝን
በመስቀል ላይ ሞተህ ከሞት ያዳንከኝን ያዳንከኝን
አዝማች · Chorus
በራ በራ በራ በራ በራ
ጨለማዬ በራ
በራ በራ በራ
ጨለማዬ በራ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ