ዕልልታ
Elelta
2012 · ትራክ 2 · 6:32 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በግብፃውያን መንደር ጨለማው በርክቷል
በእኔ ቤት ብርሃኔ ኢየሱሴ በርቷል
የጠላቴን መንገድ ሁካታ ሞልቶታል
የእኔ ግን ድንኳኔ በዕልልታ ተሞልቷል
አዝማች · Chorus
ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (4x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሲሳካም ዕልልታ
ሳይሆንም ዕልልታ
ኢየሱስ ነው ጌታ
ተራራም ዕልልታ
ሸለቆም ዕልልታ
አቀዋለሁ ጌታ
አዝማች · Chorus
ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (4x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እያልኩኝ ብውል ባድር
አይገልጥም የአንተን ክብር
እያልኩኝ በበገናዬ
ማደሪያህ ልግባ ጌታዬ
አዝማች · Chorus
ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (4x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ሆነው
የመጣህላቸው ሲዘምሩ ነው
የውህኒው መሠረት የተናወጠው
ሲቆዝሙ አይደለም በዕልልታ እኮ ነው
አዝማች · Chorus
ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (4x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ከሁኔታ በላይ የሚያዘምረኝ
ተቆጥሮ የማያልቅ ውለታ አለብኝ ኦ
ዘሬ ቢገዛለት ፍጥረትም ቢያመልከው
የእርሱን ህልውና ማነው የሚተርከው
በበጋም ዕልልታ
በክረምት ዕልልታ
አትለወጥ ጌታ
ሲዘጋም ዕልልታ
ሲከፈት ዕልልታ
አንተ ብቻ ጌታ
አዝማች · Chorus
ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (4x)
ቁጥር 6 · Verse 6
እያልኩኝ ብውል ባድር
አይገልጥም የአንተን ክብር
እያልኩኝ በበገናዬ
ማደሪያህ ልግባ ጌታዬ
አዝማች · Chorus
ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (4x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ግርማውና ክብሩ ፊቱ ይታየኛል
ነፍስም አልቀረልኝ ዕልልታ ሞልቶኛል
(እሰይ የእኔ ጌታ)
ከበሮ ይመታ ይደርደር በገና
ከጥንት ለዘለዓለም ብቻውን ገናና
አዝማች · Chorus
ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (4x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ