አንተው ነህ አቅሜ
Antew Neh Aqemie
2012 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አመታት አለፉ ዘመናትም ሄዱ
እስካሁን በቤቱ አለሁኝ
እያገለገልኩኝ/ገና እኖራለሁኝ
በቤትህ ተተክዬ እንዳፈራልህ
ታማኝ ባሪያ ሆኜ እንድኖርልህ
ለኔ ምኞቴ ነው ቀን ከሌት ፀሎቴ
በክብር እስክገባ የላይኛው ቤቴ
አዝማች · Chorus
አሜን/*8
ቁጥር 2 · Verse 2
እንደዚያች ውርንጫ በላዬ ተቀምጠህ
ስራ ስትሰራብኝ ታሪኬን ለውጠህ
ይህንን የሰማ ዲያብሎስ ቢቀና
ወዴት ያገኘኛል ዛቻው ሁሉ መና
አዝማች · Chorus
አሜን/*4
ቁጥር 3 · Verse 3
በድካም በብርታት በመውደቅ መነሳት
ከክፉ ውሳኔ ነፍሴን ስትመልሳት
ብዙ ጊዜ አየሁህ ጣልቃ ስትገባ
ድርሰህ ስታድነኝ ከጠላት ከበባ
ያኔ ካንተ ጋራ ጉዞ የጀመሩ
አሉ ብዙ ሰዎች ከኋላ የቀሩ
እኔ ይገርመኛል እስካሁን መቆሜ
ፅዮን እስክገባ አንተው ነህ አቅሜ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ