ማዳኑ ብዙ ነው
Madanu Bezu New
2012 · ትራክ 3 · 6:15 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ማዳኑ ብዙ (፯x) ነው
ብዙ (፯x) ነው
ማዳኑ ብዙ (፮x) ነው
ብዙ ነው
አዝማች · Chorus
ማዳኑ ብዙ ነው
ብዙ ብዙ ነው
ብዙ ነው (፪x)
ለእኛ ያረገው ብዙ ነው (፪x)
እናመስግነው እናመስግነው
እንስግድለት እናመስግነው
ለእኛ ያረገው እጅግ ብዙ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ድንግዝግዝ ብሎን መንገዱ ጠፍብቶን
ግራ ሲገባን
ያገኘን መስሎት ጠላት ተደስቶ
የውድቅት ወሬ ሲያሰማን
የማይጥል ጌታ ድንገት ደረሰና
ድንቅ አረገልን
ጉድጓዱን ደፍኖ ወጥመዱን ሰበረው
ለእኛስ ማምለጥ ሆነልን
አዝማች · Chorus
ማዳኑ ብዙ ነው
ብዙ ብዙ ነው
ብዙ ነው (፪x)
ለእኛ ያረገው ብዙ ነው (፪x)
እናመስግነው እናመስግነው
እንስግድለት እናመስግነው
ለእኛ ያረገው እጅግ ብዙ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እንደ በደላችን ያላረገብን የተሸከመን
ታማኝነቱ እጅጉን የበዛ
ሳይሰለች በፀጋው ያቆመን
እንዘምርለት ለውለታው ምላሽ
ብዙ ምሥጋና
ተራራም ቢንሆን ሸለቆም ብንወርድ
ያልተወን እርሱ ነውና
እናመስግነው እናመስግነው
እንስግድለት እናመስግነው
ለእኛ ያረገው እጅግ ብዙ ነው (፪x)
ለእኛ ሳይገባን ተጠነቀቀልን
ስንቴ ታደገን
የአውሬውን መንጋጋ የዘጋው እርሱ ነው
እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን
ለነገም ቢሆን በፍፁም አንሰጋም
ጌታ ታማኝ ነው
ትንፋሻችንን እና መንገዳችን ሁሉ
በእራሱ በእግዚአብሔር እጅ ነው
አዝማች · Chorus
ማዳኑ ብዙ ነው
ብዙ ብዙ ነው
ብዙ ነው (፪x)
ለእኛ ያረገው ብዙ ነው (፪x)
እናመስግነው እናመስግነው
እንስግድለት እናመስግነው
ለእኛ ያረገው እጅግ ብዙ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ