እስቲ ልዘክረው
Esti Lezekerew
2012 · ትራክ 5 · አማርኛ
የሞትክልኝ በቀራኒዮ በእንጨት ተሰቅለህ
ለማልጠቅመው ለማልረባው ለእኔ ብለህ የታደከኝ ከባለዕዳው እዳዬን ከፍለህ
እንዴት ይረሳል (2×)
ጌታ
እንዴት ይረሳል (2×)
ኢየሱስ
እንዴት ይረሳል (2×)
ውዴ
እንዴት ይረሳል (2×)
ኢየሱስ
ጨለማው በርትቶ ቀንበር ከብዶብኝ
የሀጢያት ባሪያ ሆኜ አመፅ ሰልጥኖብኝ
እንደ ስጋ ፈቃድ ስመላለስ ኖሬ ኢየሱስ በደሙ ነፃ አወጣኝ ዛሬ (2×)
እንዴት ይረሳል (2×)
ጌታ
እንዴት ይረሳል (2×)
ኢየሱስ
እንዴት ይረሳል (2×)
ውዴ
እንዴት ይረሳል (2×)
ኢየሱስ
ከሳሼ ታቅፎ የእዳውን ፅፈት
ሲደረድር ዋለ ታሪኬን በመክፈት
ኢየሱስ ግን ለኔ አዘነልኝና
ፍርዴን ወሰደልኝ ሞቴን ሞተው እና (2×)
የሞትክልኝ በቀራኒዮ በእንጨት ተሰቅለህ
ለማልጠቅመው ለማልረባው ለእኔ ብለህ የታደከኝ ከባለዕዳው እዳዬን ከፍለህ
እንዴት ይረሳል (2×)
ጌታ
እንዴት ይረሳል (2×)
ኢየሱስ
እንዴት ይረሳል (2×)
ውዴ
እንዴት ይረሳል (2×)
ኢየሱስ
የመስቀሉን ስራ እስኪ ልዘክረው
አደባባይ ልውጣ ፍቅሩን ልዘምረው
ሰይጣን የሞት መውጊያ ሲዖል ተሸነፏል
ጆሮ ያለው ይስማ ኢየሱስ ተነስቷል
ከሞት አድኖኛል
እንዴት ይረሳል (2×)
ጌታ
እንዴት ይረሳል (2×)
ኢየሱስ
እንዴት ይረሳል (2×)
ውዴ
እንዴት ይረሳል (2×)
ኢየሱስ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ