Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንደ እግዚአብሔር ያለ የለም

Ende Egziabhier Yale Yelem

ትራክ 10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

(እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም) (፪x)

እያልኩ አወራለሁ አወራለሁ በሕይወት ዘመኔ እይቻለሁ) (፪x)

እናቴ በቅርጫት ጠቅልላ ስትጥለኝ

ፈርኦንን ፈርታ ባሕር ላይ ስትተወኝ

አግዚአብሄር እጆቹን ዘርግቶ አሞቀኝ

እንዳልጠፋ እንዳልሞት አቅፎ አተረፈኝ

በድንገት ሳላውቀው ፈርኦን ቤት ገባሁ

ምንም ሳይጐልብኝ በእናቴ ጡት አደኩ

እብራይስጥ እያለሁ የግብጽ ይሁን ተባልኩ

በወግ በመዓረግ አደኩኝ በለጽኩ

ይህንን ሁሉ አለፍኩ ያን ሁሉ አዋቂ ነው

ህዝቡን አንድመራ ለካስ ላላማው ነው

(በልጅነት ዘመን ሲመራኝ (ሲያግዘኝ) እያየሁ

ማንም እንደ እግዚአብሔር አይሆንም እላለሁ) (፪x)

እንደ እግዚአብሔር ያለ

ግብጻዊውን ገድዬ በረሃ ስገባ

ውኃ ጥም ሲፈጀኝ የምበላው ሳጣ

እንዳልተከበርኩኝ ደግሞ እረኛ ስሆን

ኑሮዬን ጠልቸው ሳማርር ጌታዬን

ጭራሹን መጣና በሽምግልናዬ

እግዚአብሄር ጠራኝ እኔ በቃ ብየ

ባደኩበት ኑሮ ቤቴ ተመልሼ

ከፈርኦን ገጠምኩ በትሬን በእጄ ይዤ

ለካስ ለታሬክ ነው ጌታ ያስቀመጠኝ

ከባሕር አንስቶ በቤቱ ሊሾመኝ

(በሽምግልናዬ ሲመራኝ ሲያግዘኝ) እያየሁ

ማንም እንደ እግዚአብሔር አይሆንም እላለሁ) (፪x)

እንደ እግዚአብሔር ያለ

ይህን ሁሉ አለፍኩ ያን ሁሉ አዋቂ ነው

ህዝቡን እንድመራ ለካስ ለአላማው ነው

በልጅነት ዘመን ሲመራኝ እያየሁ

ማንም እንደ እግዚአብሔር አይሁንም እላለሁ

ለካስ ለታሬክ ነው ጌታ ያስቀመጠኝ

ከባሕር አንስቶ በቤቱ ሊሾመኝ

(በሽምግልናዬ ሲመራኝ ሲያግዘኝ) እያየሁ

ማንም እንደ እግዚአብሔር አይሆንም እላለሁ) (፪x)

እንደ እግዚአብሔር ያለ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ