Tesfaye Chala/Lebarkew Gietayien Lebarkew/Ewedehalehu Gieta
ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
(እወድሃለሁ ጌታ እወድሃለሁ የሱስ) (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በኃጢአቴ ሙታን በነበርኩ ጊዜ ሳላይህ ያየኸኝ
ሳላውቅህ አውቀኸኝ ከክርስቶስ ጋራ ሀይወትን ሰጠኸኝ
እኔ ምን እላለሁ ላመስግንህ ጌታ እጄን ልዘርጋ እንጂ
አንተ የፍቅር ጌታ ምህረትህ የማያልቅ ፍቅርህ አያረጂ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከአስፈሪው ነበልባል እወድሃለሁ ጌታ ከገሃነም ዳንኩኝ እወድሃለሁ የሱስ
እኔም እንደ ጻድቃን እወድሃለሁ ጌታ ጸድቀሃል ተባልኩኝ እወድሃለሁ የሱስ
ቁጥር 3 · Verse 3
በኃጢያቴ ምክንያት የሞትኩኝ ነበርኩኝ
እኔም በእግዚአብሔር በአምላኬ ታሰብኩኝ
የመርገም ጨርቄን ከላዬ ገፈፈው
ጽድቅን አለበሰኝ (የሚከሰኝ ማን ነው) (፪x)
አዝማች · Chorus
እወድሃለሁ ጌታ
እግዚአብሔርም ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ በኃጢአታችንና በበደላችን ሙታን በነበርን ጊዜ
ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ሕይወትን ሰጠን
ሰው ዞር ብሎ አያየኝ ቢሆንማ ኑሮ ምህረት በሰው እጅ
እንኳን ለጽድቅ ልሆን እንኳን ለሌላው ሰው ለራሴም አልበጅ
ዓይኑ እንዳየች ሳይሆን ጆሮው እንደሰማች ሳይፈርድ አጸደቀኝ
ኧረ ይገርማል ኧረ ይገርማል ሰዎች እኔንም አዳነኝ
የማይገባኝን እወድሃለሁ ጌታ የሕይወትን አክሊል እወድሃለሁ የሱስ
በነጻ ሰጠኸኝ እወድሃለሁ ጌታ ስምህ ከፍ ይበል እውድሃለሁ የሱስ
(እወድሃለሁ ጌታ እወድሃለሁ የሱስ) (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ