በራችንን ደጁን ዘግተን
Berachenen Dejun Zegten
ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
(ልባርከው ጌታዬን ልባርከው
ልባርከ እየሱሴን ልባርከው) (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በሰማዩ ስፍራ ባረክኝ
የረገጥኩትን አወረሰኝ
(ታዲያ ምኔን ልስጠው ለጌታ
እስኪ ከፍ አርጉልኝ በልልታ) (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የነገረኝን በሙሉ እስከሚያደርግልኝ ታምኖ
የክፉ ቀን መሸሸጊያ በሃሩሩ ጥላ የሆነው
ሲጠማኝ ምንጭ አፈለቀ ሲርበኝ ደግሞ አጐረሰኝ
ሰው ዓይንህ ላፈር ሲለኝ ኢየሱስ አንዴ ሳይሸሸኝ
እንደበደሌ አልከፈለኝ ምህረቱ ስለእኔ በዝቷል
በነፍስና በሥጋየ በረከቱ ቤቴን ሞልቷል
እንዴት ታዲያ ዝም ልበል ይህንን ሁሉ አይቸ
ልስገድ ልውደቅ በግንባሬ ማደሪያው ቤቱ ገብቸ
አዝማች · Chorus
ልባርከ ጌታዬን
በደሌ በፊቱ በዝቶ ያለቀ የሞትኩ ሲመስለኝ
የጠላቴ ማስፈራራት ጩኸቱ ሲያርበደብደኝ
በዘመርኩበት አንደበት ሙሾ ለመውረድ ስዳዳ
የሞትን ወሬ ሰምቸ ለነፍሴ ሞትን ላረዳ
ስዋከብ ከዚህ ወደዚያ ጭንቀቴን አይቶ ደረሰ
የተዋጋኝን ተዋጋው እቅዱን አፈራረሰ
ዛሬማ በኮረብታ ላይ ቆሜ ምሥጋና እሰዋለሁ
ሰው ያደረገኝን አምላኬን በዜማ እባርካለሁ
ልባርከው ጌታዬን
ቁጥር 4 · Verse 4
በሰማያዊ በረከት በመንፈስ ባርኮ ባረከኝ
የምድሩንም አላጣሁም ይልቁን አትረፈረፈኝ
ሳይሰለች የተሸከመኝ ቀን በቀን ቤቴን ባረከው
ዓለም የነፈገችኝን ኢየሱስ እጥፍ አረገው
ኢየሱስን ብሎ ወዝ አጣ ያሉኝ ዛሬ አፈሩ
ጌታ ሞገሴ መሆኑን በአፋቸው መሰከሩ
ወጥመድ ቢዘጋጂልኝም ኢየሱስ እየቀደመ
ሕይወቴን በረከት ሞላው ደረቅ በትር ለመለመ
አዝማች · Chorus
ልባርከው ጌታዬን
ቁጥር 5 · Verse 5
እናንተም እንደኔው ጌታ በቀን በቀን የባረካችሁ
በተሰደዳችሁበት ምድር እጅግ ያበዛችሁ
የገዛችሁን ኢየሱስ ከግራችሁ ያስገዛላችሁ
ጂራት ሳይሆን እንደቃሉ የሁሉ ራስ ያረጋችሁ
እስኪ እናንተው ንገሩኝ ለኢየሱስ ምን ይከፈላል
ወደር ለሌለው ምህረቱ ምን ምላሽ ምንስ ይሰጣል
ከአድማስ እስከ አድማስ ሙገሳ ክብር ሙገሳ ይድረሰው
ፍጥረት ሁሉ ይህን ጌታ በአንደበቱ ይቀድሰው
አዝማች · Chorus
ልባርከው ጌታዬን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ