ሥልጣን የአንተ ጌታዬ ሆይ
Seltan Yeante Gietayie Hoy
ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንተን ጠርቶ ማን አፈረ
ተማምኖብህ ማን ከሰረ
የተዘጋውን ትከፍታለህ
የታሰረውን ትፈታለህ
የታመመውን ታድናለህ
የሞተውን ታስነሳለህ
ቁጥር 2 · Verse 2
(ስልጣን ያንተ የእኔ ጌታ ስልጣን የአንተ
ስልጣን የአንተ ጌታዬ ሆይ ስልጣን የአንተ) (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ባሕር መክፈል ትችላለህ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ
በር ሲዘጋ ትመጣለህ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ
የችግረኛውን ጩኸት የምትሰማ
የክፉ ቀን ወዳጅ ኢየሱስ ብርሃን በጨለማ
እስከዛሬስ ማንን ጥለህ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ
ቢመኩብህ ታስመካለህ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ
ቁጥር 4 · Verse 4
(ቢመኩብህ ታስመካለህ) (፬x)
አዝማች · Chorus
አንተን ጠርቶ
ቁጥር 5 · Verse 5
መርከቢቱ ስትናወጥ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ
ልብም ሲርድ ሲንቀጠቀጥ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ
በድንገት ብቅ ብለህ ማዕበሉን ገሰጽከው
ለአምላክነትህ ኢየሱስ ፍጥረት ምስክር ነው
እኛንም ከሕይወት ማዕበል ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ
ስንት ጊዜ አሳረፍከን ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ
ቁጥር 6 · Verse 6
(ስንት ጊዜ እረዳኸን ስንት ጊዜ አሳረፍከን) (፪x)
አዝማች · Chorus
አንተን ጠርቶ
ቁጥር 7 · Verse 7
የሞተው ሲታዘዝልህ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ
ታላቁ ሰው ሲሰግድልህ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ
በዝች አጭር ዕድሜ ብዙ ጊዜ አይተናል
ሳይወድ በግዱ ፍጥረት ለአንተ ይገዛል
ማንስ ሊቆም ከአንተ ጋራ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ
ለሚያምኑበት የሚያኮራ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ
ቁጥር 8 · Verse 8
(ለሚያምኑበት የሚያኮራ) (፬x)
አዝማች · Chorus
አንተን ጠርቶ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ