Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የአምላኬን ቤት

Yeamlakien Biet

ትራክ 2 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የአምላኬን ቤት ጠላት ሲወርሰው

ሰውም ለራሱ መኖር ሲመቸው

ጠባቂው ሸሽቶ ሁሉም ሲተኛ

መንጋው ሲበተን ጠፍቶ እረኛ

አንጀቴን ልሰር ምግብ አልብላ

ነግ ይሆናል ፍርዱ በኋላ

የአምላኬ ባሮች አስኪ ተነሱ

ለፈረሰው ቅጥር ኑና አልቅሱ

ልመለስ ልግባ ወደ እልፍኜ

ልንቃና ልማልድ ተረድቼ

የደከምኩ ያረጀሁ ቢመስለም

በአምላኬ እኔስ ተስፋ አልቆርጥም

ዓይኖቼ ፈዘው በቅጡ ሳላይ

ጠላት ሲሳሳቅ በአምላኬ ቤት ላይ

ከተኛሁበት ድንገት ስነቃ

ቅናቱ በላኝ ሆነኝ ሰቆቃ

ጉልበቴን ጠላት በልቶት ቢስቅም

መውደቄን ሰምቶ ቢጠቋቆምም

ወድቄ አልቀርም ደግሞ እነሳለሁ

የአምላኬን ቅጥሩን አሳምራለሁ

ልመለስ

ማን ወድቆ ቀርቷል ሳያንሰራራ

የጠላቶቹን ጡጫ እንደፈራ

ባለቀ ስአት መድረስ የሚያውቀው

ታማኙ አምላኬ ከእኔ ጋራ ነው

የጠላቱን ቤት መትቶ ያፈርሳል

የእርሱ የሆኑትን ጌታ ያጠራል

ጸሎቴን ሰምቶ ይጐበኘኛል

የሱስን ይዤ ምን ያሰጋኛል

ልመለስ

በአባቴ ቤት ሸቀጡ በዝቶ

ሁሉም ሊነግድ ያለውን አምጥቶ

መደቡን ሰርቶ ሰው ቢመቻችም

ኢየሱስ ይሄንን ዝም ብሎ አያይም

ጌታ ጅራፉን ይዞ ይነሳል

የቤቱን ጉድፍ ጠርጐ ይስወጣል

የሳቀ ጠላት በተራው ያፍራል

የክብሩ ቤት ግን ገና ያበራል

ልመለስ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ