እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ
Eniem Ethiopiawi Negn
ትራክ 6 · 5:58 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዙ እንቆቅልሽ አለኝ
ጌታ አንተ ንጉሥ ነህ እንቆቅልሽን መፍታት ታውቃለህ
የዕውቀት የጥበብ ጌታ እንቆቅልሼን ፍታ
ቁጥር 1 · Verse 1
በዛና እንቆቅልሼ ለብዙ ዘመን አልቅሼ
አንድ ቀን ዝናህን ሰማሁ ልነግርህ ከሳባ መጣሁ
ተቀመጥ በዙፋንህ የልቤን እንድነግርህ
አዝማች · Chorus
እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዙ እንቆቅልሽ አለኝ
ጌታ አንተ ንጉሥ ነህ እንቆቅልሽን መፍታት ታውቃለህ
የዕውቀት የጥበብ ጌታ እንቆቅልሼን ፍታ
ቁጥር 2 · Verse 2
በግመል ሽቱ ጭኛለሁ ወርቅና ዕንቁም ይዣለሁ
ደክሞኛል ጓዜ ብዙ ነው አድምጠኝ ያኔ አርፋለሁ
አገሬን በዚህ ወክዬ ከእግርህ ስር ልውደቅ ጌታዬ
አዝማች · Chorus
እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዙ እንቆቅልሽ አለኝ
ጌታ አንተ ንጉሥ ነህ እንቆቅልሽን መፍታት ታውቃለህ
የዕውቀት የጥበብ ጌታ እንቆቅልሼን ፍታ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሠማይና ምድርን ፈጥረሃል በጥበብህ ሁሉን አድርገሃል
ከዓይንህ የተሰወረ አሸንፎህስ የኖረ
ንጉሥ ሆይ ኧረ ምን ነበር ፍታልኝ የእኔንም ነገር
አዝማች · Chorus
እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዙ እንቆቅልሽ አለኝ
ጌታ አንተ ንጉሥ ነህ እንቆቅልሽን መፍታት ታውቃለህ
የዕውቀት የጥበብ ጌታ እንቆቅልሼን ፍታ
ቁጥር 4 · Verse 4
ገና ጥንት ሳለሁ በአገሬ ስለ አንተ የሰማሁት ወሬ
ማመን ግን አቅቶኝ ነበር ልክ የለው የዕውቀትህ ነገር
ጥበብህ ከአእምሮ ያልፋል ከሰማሁት ዝናህ ይበልጣል
አዝማች · Chorus
እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዙ እንቆቅልሽ አለኝ
ጌታ አንተ ንጉሥ ነህ እንቆቅልሽን መፍታት ታውቃለህ
የዕውቀት የጥበብ ጌታ እንቆቅልሼን ፍታ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ