ምሥጋና
Mesgana
ትራክ 4 · 2:53 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሃሌሉያ : ሃሌሉያ : ሃሌሉያ
አሳዳጃችን ከባሕር ሰጥሞ
ምድረ በዳችን በአንተ ለምልሞ
ከያለንበት ተሰብስበናል
እኛም ሰው ሆነን ሰውን ማርከናል
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ከአእምሮያችን በላይ ለሆነው ውለታህ
ቆጥረን እስከማንዘልቅ ለበዛው ስጦታህ
እናከብርሃለን ክበርልን ጌታ
ቁጥር 2 · Verse 2
በሰው ልጅ ኀጢአት ምድርን ብትቀጣ
የመከራ ጐርፍ ከላይ ቢመጣ
በዙሪያችን አጥር ሰርተሃል
ለእኛ ለሕዝብህ መርከብ ሆነሃል
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ከአእምሮያችን በላይ ለሆነው ውለታህ
ቆጥረን እስከማንዘልቅ ለበዛው ስጦታህ
እናከብርሃለን ክበርልን ጌታ
ቁጥር 3 · Verse 3
የፈርኦን ጦር ሕዝቡን አሳዶ
እርሱ ግን ቀረ ከባሕር ማዶ
እርስታችንን በድል ወርሰናል
በአንተ እረኝነት እዚህ ደርሰናል
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ከአእምሮያችን በላይ ለሆነው ውለታህ
ቆጥረን እስከማንዘልቅ ለበዛው ስጦታህ
እናከብርሃለን ክበርልን ጌታ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ