ወደ አባቴ እመለሳለሁ
Wede Abatie Emelesalehu
ትራክ 1 · 8:17 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የተወደዳችሁ አድማጮቼ ፣
ከዚህ ቀጥሎ የምታደምጡት መዝሙር
በሉቃስ ወንጌል ምእራፍ ፲፭ ከቁጥር ፲፩ - ፳፬
ድረስ በተፃፈው የኮብላይ ልጅ ታሪክ የተወሰደ
መሆኑን እያስታወስኩ በዚህ ታሪክ ምሳሌነት
የእግዚአብሔር ን አባታዊ እና ዘለዓለማዊ ፍቅር
አሳስባችኋለሁ በምታደምጧቸው ዝማሬዎች ሁሉ
እግዚአብሔር ይባርካችሁ አሜን
አዝማች · Chorus
ወደ አባቴ ወደ ቀድሞ ቤቴ እመለሳለሁ
እንደ ልጁም ባይሆን እንደ ባሪያው እኖራለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
መስሎኝ ነበር እኔ እራሴን የገዛሁ
ንብረቴን ሰብስቤ ሩቅ ሃገር ተነሳሁ
ለካስ ልጅ ኖሬያለሁ ምራቄን ያልዋጥኩኝ
ለወፍ ለአሞራ ያለኝን በተንኩኝ
ጉልበቴም ደከመ ሕይወቴም ባከነ
ለካስ አባት ኖሮዋል ጉዴን የሸፈነ
አዝማች · Chorus
ወደ አባቴ ወደ ቀድሞ ቤቴ እመለሳለሁ
እንደ ልጁም ባይሆን እንደ ባሪያው እኖራለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ወዳጄ ነበረ ካለኝ ያካፈልኩት
ያጣሁ የነጣሁ እለት ከቦታው አጣሁት
ሁሉም በር ዘግቶ አላውቅህም አለኝ
የሚያዝንልኝ አጣሁ ሰው ሁሉ አገለለኝ
አየሁ ተገነዘብኩ ወዳጅ ማንነቱን
ማን ይሆንለታል ለሰው እንደ አባቱ?
አዝማች · Chorus
ወደ አባቴ ወደ ቀድሞ ቤቴ እመለሳለሁ
እንደ ልጁም ባይሆን እንደ ባሪያው እኖራለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሰርቼ እንዳልበላ ጨርሶ የለኝ ሞያ
ተደብቄ ኖርኩኝ በአባቴ ጉያ
ጉዴ ተገለጠ ታየ ገበናዬ
ከእሪያዎች ጋር ሆነ መዋያዬ
ዘበኝነት አጣሁ ጠፋኝ መላ ቅጡ
ለካስ ማእረግ የለም ከአባት ቤት ከወጡ
አዝማች · Chorus
ወደ አባቴ ወደ ቀድሞ ቤቴ እመለሳለሁ
እንደ ልጁም ባይሆን እንደ ባሪያው እኖራለሁ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
እኔን ያየኝ ይቀጣ ይማር ከሕይወቴ
እርቃናዬን ቀረሁ በአባካኝነቴ
ሳለሁ ባባቴ ቤት ወዜን ያየ ማነው?
ያስብ ጠንቀቅ ይበል
ይህ ዓለም ክፉ ነው አጫርሶ ዝም ይላል
ምንም ይሁን ምንም የአባት ቤት ይሻላል
አዝማች · Chorus
ወደ አባቴ ወደ ቀድሞ ቤቴ እመለሳለሁ
እንደ ልጁም ባይሆን እንደ ባሪያው እኖራለሁ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
አዋጅን የምትሰማ ያለህ የትም ቦታ
ጨለማ የዋጠህ የጠፋህ ከጌታ
እንጀራውን በልተህ ፈውሱን ተቀብለህ
ድርሻህን በመውሰድ የሄድከው ኮብልለህ
እስኪ መለስ በል ወደ ጥንቱ ቤትህ
አይጨክንብህም ርህሩህ ነው አባትህ
ለጣትህ ቀለበት ለእግርህ ጫማ
ያጐናፅፍሃል በመንፈሱ ሸማ
ፍሪዳ ይታረድ ወገን ደስ ይበለው
ለነገ አታሳድር መዳንህ ዛሬ ነው
አዝማች · Chorus
ወደ አባቴ ወደ ቀድሞ ቤቴ እመለሳለሁ
እንደ ልጁም ባይሆን እንደ ባሪያው እኖራለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ