Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ማን ነው ያነጋው

Man New Yanegaw

5:39 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

(ማነው ያነጋው ሌሊቱን? ማነው ያጠፋው እሳቱን?

(ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ) ፪X (፪X)

በአንድ መንገድ የመጡ በብዙ በሺህ ሲወጡ

እየወደቁ ሲነሱ ክብርን ለጌታ ሲሰጡ

የናቀኝ ሁሉ ሲያከብረኝ በክብር ስሜ ሲጠራኝ

ዕድሜ ሰጥተኸኝ አየሁኝ (ያንተ መሆኔ አኮራኝ) ፪X

(ማነው ያነጋው ሌሊቱን? ማነው ያጠፋው እሳቱን?

(ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ) ፪X (፪X)

ከባቢሎን ወንዞች ማዶ ከምርኮ ከስር ከተማ

የመውጣት ነገር ሲነገር የነፃነት ድምፅ ሲሰማ

ደወል ሲመታ በድንገት ኧረ የማን ልብ አመነ?

ምን ያቅትሃል ጌታችን? (አንተ ስላልከው ግን ሆነ) ፪X

(ማነው ያነጋው ሌሊቱን? ማነው ያጠፋው እሳቱን?

(ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ) ፪X (፪X)

በባእድ ምድር እያለን የታመቀውን እሳት

ጌታ ሊያነደው ጀመረ አዲስን ምእራፍ ሊከፍት

ከዛፍ ወረደ ማሲንቆ ከዛፍ ወረደ በገና

የፅዮን ዝማሬ ልንዘምር (አዲሱን ቅኔ ምሥጋና) ፪X

(ማነው ያነጋው ሌሊቱን? ማነው ያጠፋው እሳቱን?

(ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ) ፪X (፪X)

እያለቀስን ወጥተናል በሃዘን ዘርን ዘርተናል

በምድር በሠማይ መካከል እንባችንን ረጭተናል

የዜማ ጊዜ ደረሰ ነዶአችንን ይዘን መጥተናል

በውዳችን ተደግፈን (ከምድረ በዳ ወጥተናል) ፪X

(ማነው ያነጋው ሌሊቱን? ማነው ያጠፋው እሳቱን?

(ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ) ፪X (፪X)

ጌታ ምርኮያችንን ሲመልስ ለቅሶ በመዝሙር ሲተካ

ቃላችን ውስን ምድራዊ ደስታችን በምን ይለካ?

አፋችንን በሳቅ ሞላ አንደበታችን ምሥጋና

ሁሉን ውብ አድርጓል (የታሪክ ጌታ ነውና) ፪X

(ማነው ያነጋው ሌሊቱን? ማነው ያጠፋው እሳቱን?

(ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ) ፪X (፪X)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ