ኢየሱስ ገናና ነው
Eyesus Genana New
ትራክ 2 · 10:21 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክብሩን ሁሉ ትቶ ከሠማይ ወረደ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
የሰው ሥጋ ለብሶ ራሱን አዋረደ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
የእግዚአብሔር በግ ሆኖ በረት ተወለደ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
የዋህ ትሁት ሆኖ እንደ በግ ታረደ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ፈራጅ በሌለበት እውነተኛ ዳኛ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
የውርደት ሞት ሊሞት እንደወንጀለኛ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
በደሙ ቢነከር ቀራንዮ ተራራ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
መቃብሩም ቢሆን ከአመፀኞች ጋራ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
በሞተ ሰልስቱ ታሪክ ተለወጠ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
አይሰማ ሰምቶ ዓለም ደነገጠ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
መቃብሩን ከፈተ ማኅተሙን ፈታ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ሞትን ድል አረገ የትንሳኤው ጌታ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
አዝማች · Chorus
ገናና ኢየሱስ ገናና (፬x)
ተወዳዳሪ የለውምና
አቻ የሚሆነው የለውምና
ገናና ኢየሱስ ገናና (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የሞት መርዶ ሰምተው በሃዘን የተዋጡ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
በትንሳኤው ብስራት ዕልልታ አቀለጡ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
አጠፋነው ብለው የዘፈኑ ሁሉ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ትንሳኤውን ሲሰሙ ምድር ዋጪን አሉ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
በኢየሱስ ሰፈር ዕልልታ ሲሰማ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
በዲያብሎስ ሰፈር የሃዘን ጨለማ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ከማሪያም ጀምሮ እስከ ቶማስ ድረስ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
በዐይን በማየት ደግሞም በመዳሰስ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ኢየሱስ መነሳቱን አረጋገጡልን
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ይህን ክቡር ታሪክ ፅፈው አስቀሩልን
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
አምነን የተቀበልን እኛም ተነስተናል
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
በኢየሱስ ትንሳኤ ሞትን እረግጠናል
አዝማች · Chorus
ገናና ኢየሱስ ገናና (፬x)
ተወዳዳሪ የለውምና
አቻ የሚሆነው የለውምና
ገናና ኢየሱስ ገናና (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የኢየሱስ ጌትነት በዚህ አላበቃም
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ገና ይቀጥላል ታሪክ አልተዘጋም
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ከትንሳኤው ኋላ አርባ ቀናት ኖሮ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
የቤተ ክርስቲያን መሰረት አኑሮ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ሰው ሆኖ የመጣው ጌታ ሆኖ ሄዷል
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
በውርደት የመጣው በክብር አርጓል
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ዛሬም ሕያው ሆኖ በአብ ቀኝ አለልን
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
እያማለደልን ቤት እየሰራልን
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ያኔ መጀመሪያ በግ ሆኖ የመጣው
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ዳግም ሲመለስ ግን የጌታዎች ጌታ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
በመለከት ድምፅ በመላእክት አጀብ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
አብረን እንድንገባ ቶሎ እንመዝገብ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ስለስሙ ብለው የተገፉ ሁሉ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ኢየሱስ ሲከብር አብረው ይከብራሉ
አዝማች · Chorus
ገናና ኢየሱስ ገናና (፬x)
ተወዳዳሪ የለውምና
አቻ የሚሆነው የለውምና
ገናና ኢየሱስ ገናና (፫x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ዛሬም በዚህ ዘመን በሕይወቱ እያለ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ካልካደ በስተቀር ያላየ ማን አለ?
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ክህደትን አመፅን ከምድር ሲያጠፋ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
የእግዚአብሔር መንግሥት ድንበሯ ሲሰፋ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
በኢየሱስ ስም ስልጣን ወንጌሉ ሲሰበክ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ምላስ ሲመሰክር ጉልበት ሲንበረከክ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ታዲያ ለምንድነው ወገኔ የምትደክም?
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ሕያው አምላክ እንጂ ግኡዝ አታመልክም
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
በዚህ አጭር ዘመኔ ኧረ ስንት አሳየኝ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ለኢየሱስ ጌትነት እኔም ምስክር ነኝ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
አንቺም ምስክር ነሽ አንተም ምስክር ነህ
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
ሁላችንም እንበለው ኢየሱስ ጌታ ነው
ኦ ገናና ነው ፣ ኦ ኢየሱስ ገናና
አዝማች · Chorus
ገናና ኢየሱስ ገናና (፬x)
ተወዳዳሪ የለውምና
አቻ የሚሆነው የለውምና
ገናና ኢየሱስ ገናና (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ