ማራናታ
Maranatha
ትራክ 8 · 4:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በአዲስ ሕይወት ኑሮ ከአንተ ጋር
በሰላም በደስታ በፍቅር
ኑሮ ናፍቄያለሁ ጌታዬ
ቶሎ ና አንተ ነህ ተስፋዬ
ኦሆሆሆሆሆሆሆ
አዝማች · Chorus
ማራናታ ማራናታ
አሜን ጌታ ኢየሱስ ቶሎ ና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ባልተሰማ ቋንቋ ልናገር
ከቅዱሳኖች ጋራ ልዘምር
ይሄ ነው ናፍቆቴ ቶሎ ና
ውዴ ሆይ ኩራቴ አንተ ነህና
ኦሆሆሆሆሆሆሆ
አዝማች · Chorus
ማራናታ ማራናታ
አሜን ጌታ ኢየሱስ ቶሎ ና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አዲሱን ነኝ ለብሼ
የታረድከውን በግ ዳስሼ
ይህን ለማየት ነው ናፍቆቴ
እባክህ ቶሎ ና አባቴ
ኦሆሆሆሆሆሆሆ
አዝማች · Chorus
ማራናታ ማራናታ
አሜን ጌታ ኢየሱስ ቶሎ ና (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የምድሩ ኑሮዬ ከአንተ ጋር
ጠቅሞኛል ጌታዬ ይኸው ልናገር
ግን አሁን ናፍቆቴ ይሄ ነው
ማራናታ ጌታ ነው የምለው
ኦሆሆሆሆሆሆሆ
አዝማች · Chorus
ማራናታ ማራናታ
አሜን ጌታ ኢየሱስ ቶሎ ና (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ