አንቺ ቤተልሔም
Anchi Bethlehem
ትራክ 6 · 5:22 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሕዝቡን ከኃጢአት ሚያድን ሚፈውስ
ድንቅ መካር ኃያል ስሙም ኢየሱስ
የእስራኤል መሪ ታላቁ መስፍን
በቤተልሄም ተወለደልን (፪x)
አዝማች · Chorus
አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ ከተማ
ለዓለም የምሥራች ከአንቺ ዘንድ ተሰማ
አሜን
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰባሰገል መጡ ከነበሩበት
ለተወለደው ህጻን ሊሰግዱለት
የአዲስ ኪዳን በግ ታላቁ ጌታ
ከላይ ወረደ ሕዝቡን ሊፈታ
ሊሆን ደስታ
አዝማች · Chorus
አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ ከተማ
ለዓለም የምሥራች ከአንቺ ዘንድ ተሰማ
አሜን
ቁጥር 3 · Verse 3
ዝማሬ በመላእክት አስተጋባ
እጣንና ከርቤም በበረት ገባ
በምድር ቅጥርም ውስጥ ጽድቅም ይሆናል
እግዚአብሔር ዓለሙን እንዲሁ ወዷል (፪x)
አዝማች · Chorus
አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ ከተማ
ለዓለም የምሥራች ከአንቺ ዘንድ ተሰማ
አሜን
ቁጥር 4 · Verse 4
ታናሽ ከተማ ቤተልሔም ሆይ
መድሃኒት ከአንቺ ወጥቶ የለም ወይ
ክብር ምሥጋና ውዳሴ ስግደት
ለህጻኑ ኢየሱስ እናቅርብለት (፪x)
አዝማች · Chorus
አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ ከተማ
ለዓለም የምሥራች ከአንቺ ዘንድ ተሰማ
አሜን
ቁጥር 5 · Verse 5
ኮኮብ ይወጣል በትር ይነሳል
ለእስራኤል መዳን ይሆንለታል
ተብሎ ተነግሮ ነበር አሁን ግን ሆኗል
አምላክ ከሕዝቡ ጋራ ሊታረቅ ወዷል (፪x)
አዝማች · Chorus
አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ ከተማ
ለዓለም የምሥራች ከአንቺ ዘንድ ተሰማ
አሜን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ