ፊትህ እንቀርባለን ይኸው ዛሬ
Fiteh Enqerbalen Yehew Zarie
ትራክ 2 · 4:44 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በረሃ ነው ደረቅ ምድረ በዳ
ውስጡ ግን አበበ ጽጌሬዳ
በደስታ በሃሴት በዝማሬ
ፊትህ እንቀርባለን ይኸው ዛሬ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ማን ተስፋ ያደርጋል ጽጌሬዳ
ጨው ባለው ደረቅ ምድረ በዳ
እግዚአብሔር ሁሉን ሲያስተካክለው
አይቻለሁ አኔ ለበጐ ነው (፭x)
አዝማች · Chorus
በረሃ ነው ደረቅ ምድረ በዳ
ውስጡ ግን አበበ ጽጌሬዳ
በደስታ በሃሴት በዝማሬ
ፊትህ እንቀርባለን ይኸው ዛሬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አሁንስ ተስፋዬ ተሟጠጠ
ቢመስለኝ ያለቀ የተቆረጠ
በጊዜው መጥቶ ውብ አድርጐታል
ለእግዚአብሔር ምንድን ይሳነዋል (፭x)
አዝማች · Chorus
በረሃ ነው ደረቅ ምድረ በዳ
ውስጡ ግን አበበ ጽጌሬዳ
በደስታ በሃሴት በዝማሬ
ፊትህ እንቀርባለን ይኸው ዛሬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ምንተስኖህ ጌታ ምን ያቅትሃል
ለሰው የማይቻል ይቻልሃል
ታላቁን ተራራ ስትንደው
የተመለከተ ምስክር ነው (፭x)
አዝማች · Chorus
በረሃ ነው ደረቅ ምድረ በዳ
ውስጡ ግን አበበ ጽጌሬዳ
በደስታ በሃሴት በዝማሬ
ፊትህ እንቀርባለን ይኸው ዛሬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ