አቤኔዘር
Abenezer
ትራክ 4 · 6:28 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር
እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል
እንደተለመደው ድንቅ አድርጐልናል
ባሕሩንም ከፍሎ አሻግሮናል አቤኔዘር (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አናልፈውም ብለን አለፍነውን የመከራው ዓይነት ብዙ ነው
መች ተሸንፈን እናውቃለን አሸናፊዎች እንበልጣለን
ይህ ያልፋል ብለን ያልገመትነው የእኛ ታሪካችን ብዙ ነው
እያለፍን በድል ጐዳና አሸበረቅን በምሥጋና
አዝማች · Chorus
አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር
እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል
እንደተለመደው ድንቅ አድርጐልናል
ባሕሩንም ከፍሎ አሻግሮናል አቤኔዘር (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በሃሩር ጊዜ ሆኖ ጥላ በፍላጻ ሁሉ ከለላ
ልጆቹን ፊት ፊት እየመራ ደርሰናል ጺዮን ተራራ
የድካሙ ጊዜ አብቅቶ በብርታት ሕይወት ተተክቶ
በሽብሸባ ፊቱ ዘለናል እስካሁን ድረስ ረድቶናል
አዝማች · Chorus
አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር
እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል
እንደተለመደው ድንቅ አድርጐልናል
ባሕሩንም ከፍሎ አሻግሮናል አቤኔዘር
ቁጥር 3 · Verse 3
አሁን ከእኔ ጋራ ያላችሁ አቤኔዘር የሆነላቹህ
በፊቱ ቅረቡ በዕልልታ ሥሙ ይባረክ የእኛ ጌታ
ከአመድ ከትቢያ ያነሳቹህ በዚህ ጉባኤ ስንቶች ናችሁ
ታዲያ ለምን ነው ዝምታ የታል ደስታችሁ ለዚህ ጌታ
አዝማች · Chorus
አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር
እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል
እንደተለመደው ድንቅ አድርጐልናል
ባሕሩንም ከፍሎ አሻግሮናል አቤኔዘር
ቁጥር 4 · Verse 4
ይህ ያልፋል ብለን ያልገመትነው የእኛ ታሪካችን ብዙ ነው
እያለፍን በድል ጐዳና አሸበረቅን በምሥጋና
እንዲያ ሚከሰን ጠላታችን አሁን የታለ ከፊታችን
ኢየሱስ ስለነገሠ በጠንካራው ክንድ ተደቆሰ
አዝማች · Chorus
አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር
እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል
እንደተለመደው ድንቅ አድርጐልናል
ባሕሩንም ከፍሎ አሻግሮናል አቤኔዘር (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ