የእግዚአብሔር ምህረቱ ብዙ
Yegziabhier Meheretu Bezu
ትራክ 3 · 5:24 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የእግዚአብሔር ምህረቱ ብዙ
ደካሞችንም ማገዙ
በጀርባው አዝሎ መሸከሙ
ከኃጢአት ማንጻት በደሙ (፪x)
አዝማች · Chorus
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ጌታ ሆይ
ለዚህ ያደረስከኝ አንተ አይደለህም ወይ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔስ አይቻለሁኝ ፍቅሩን
ከፋንድያ ላይ ማንሳቱን
ዛሬ ሰው ሆኜ እዘምራለሁ
ለዚህ ክብር በቅቻለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ጌታ ሆይ
ለዚህ ያደረስከኝ አንተ አይደለህም ወይ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እጅግ ተንቄ በሰው ዘንድ
ተጥዬ ነበር በአመድ
ግን ጌታ ኢየሱስ ፈልጐኝ
ከኃጢአት/ከጅግር ማጥ ውስጥ አወጣኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ጌታ ሆይ
ለዚህ ያደረስከኝ አንተ አይደለህም ወይ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አይገርማችሁም ወይ ወገኖች
የልዑል አምላክ ባሪያዎች
ተነሱ ዘምሩ ለጌታ
እጅግ ብዙ ነው ውለታው (፪x)
አዝማች · Chorus
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ጌታ ሆይ
ለዚህ ያደረስከኝ አንተ አይደለህም ወይ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ