Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መባረክ

Mebarek

2019 · ትራክ 8 · 5:22 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያረፌ ሰዉ በጌታ ላይ የተመካ

ከቶ አይሰጋም አያስፈራው ክረምት በጋ

መቸ ፈራ ልቤ አልደነገጠም

ያባቶቼ አምላክ መች ተለወጠ

ኪዳኑ ጽኑ አይታጠፍም

ደሞ እንደልማዴ አልኩኝ እርፍ

በማለዳ በምሽቱ እዘምራለሁ በቸርነቱ

ባንደበተ ሞልቷል ምስጋና በህይወት መኖረ በርሱ ነውና

አላልፈውም ብዬ ደምድሜ ነበረ

የሞቱንም አዋጅ ጌታዬ ሰባበረ

ታምር በስቶብኛል የማወራው አለኝ

መባረክ አይደክመውም መዘመር አይደክመኝ

አገር ሰላም ሁሉ ደና ነው

ነገሬ ሁሉ በርሱ ነው ያለው

ተዘልዬ በጥበቃው ስር

እኖራለው ሳልሸባበር

አላልፈውም ብዬ ደምድሜ ነበረ

የሞቱንም አዋጅ ጌታዬ ሰባበረ

ታምር በስቶብኛል የማወራው አለኝ

መባረክ አይደክመውም መዘመር አይደክመኝ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ