ጩህ ጩህ ይለኛል
Yehulie
2019 · ትራክ 6 · 5:24 · አማርኛ
ፍቅር የጎደለበት ባግባቡ እንኳን ያልኖረ
አይዞ ባይ ወገን የሌለው ብቸኛ የነበረ
ያለበት ድረስ መተህ ወድሃለው ስትለው
ልቡን ከማፍሰስ በቀር ምንስ ሌላ አማራጭ አለው
መመኪያዬ (X3) አንተው ነህ ጌታዬ (X2)
ላፍታ ሳትለየኝ በድካም ሆነ በብርታት
ስንት ግዜ ረዳኀኝ ባሳለፍኳቸው አመታት
ልቤን ኩራት አለው ዘንድሮም ተመካብህ
የማትለዋወጥ የህይወቴ ዋስትና ነህ
የሁሌ ነህ የሁሌ አምላኬ ነህ የሁሌ
አፍቃሪ ወረት የለብህ ውዴ ልበልህ እንዳመሌ
ማይዘነጋ ነው አይጠፋም ከሃሳቤ
ሁሌ ድቅን ይልብኛል ፍቅርህ ታትሟል በልቤ
ብዙ ወጀብ አልፎ ትኩሳቱ እንደው አይበርድም
ዛሬም አንተኑ ይለኛል አይለውጥህም በማንም
የሁሌ ነህ የሁሌ አምላኬ ነህ የሁሌ
አፍቃሪ ወረት የለብህ ውዴ ልበልህ እንዳመሌ
ማይዘነጋ ነው አይጠፋም ከሃሳቤ
ሁሌ ድቅን ይልብኛል ፍቅርህ ታትሟል በልቤ
ብዙ ወጀብ አልፎ ትኩሳቱ እንደው አይበርድም
ዛሬም አንተኑ ይለኛል አይለውጥህም በማንም
የሁሌ ነህ የሁሌ አምላኬ ነህ የሁሌ
አፍቃሪ ወረት የለብህ ውዴ ልበልህ እንዳመሌ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ