መበርቻዬ
Meberchayie
2019 · ትራክ 10 · 5:43 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የነጠፈው ሸለቆ ምንም ውኃ የለለበት
ስንቱ ጠጥቶት ረካ ተዓምር ሰሪው ሲገኝበት
እሬት ሬት ያለው ሕይወት ሲቀምሱት ጣፈጠ
አንተ እጅ ላይ ሲገባ ሁሉም ነገር ተለወጠ
አዝማች · Chorus
ስደክም እያበረታኝ ሳዝንም እያጽናናኝ (2x)
እግዚአብሔር እኔ አለው እያለ ሳይለየኝ ከእኔ ጋራ ዋለ
እግዚአብሔር በቂ ነኝ እንዳለ ክረምት በጋ ከእኔ ጋራ ዋለ
ቁጥር 2 · Verse 2
መበርቻ መበርቻዬ መበርቻ መበርቻዬ
መበርቻዬ (3x) አንተው ነህ ጌታዬ
መጽናኛዬ (3x) እየሱስ ጌታዬ
ቁጥር 3 · Verse 3
በራድ አይደል ወይ ትኩስ እንድሁ ለብ ያለ
ለጌታው መኖር እያቃተው ህይወቱ የሰለለ
የፍቅሩ ጥልቀት እንጂ እስካሁን መሰንበቱ
እንደዝያማ ባይሆን ኖሮ ቁርጥ ነበር መጠፋቱ
አዝማች · Chorus
ስደክም እያበረታኝ ሳዝንም እያጽናናኝ (2x)
እግዚአብሔር እኔ አለው እያለ ሳይለየኝ ከእኔ ጋራ ዋለ
እግዚአብሔር በቂ ነኝ እንዳለ ክረምት በጋ ከእኔ ጋራ ዋለ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ