Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መልሰን

Melesen

2012 · ትራክ 9 · 4:54 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንተ ስትናገር (ላለመስማት ብለን)፪

እንዳንቀበለው (ምክንያት ደርድረን)፪

በሃጥያታችን መጠን (ልባችን ከፋና)፪

ለአንተ እሺ እንዳይል (አፈገፈገና)፪

አቤት መልሰን

መልሰን መልሰን

ከሄድንበት ርቀን(፪)

ይገርማል እሩቅ ሄደናል

ይገርማል ደጃፍ ደርሰናል

ሳናስቀድምህ ተሸንፈናል(፪)

ልባችን ተሞልቷል (በዚህች ዓለም ነገር)፪

ክፉ አስገብተናል (አንተን አስወጥተን)፪

ለጆሮ የሚጥሙ (አሉ የሚያበሉን)፪

እንደመሻተችን (የሚያስተምሩን)፪

አቤት መልሰን

መልሰን መልሰን

ከሄድንበት ርቀን(፪)

ይገርማል እሩቅ ሄደናል

ይገርማል ደጃፍ ደርሰናል

ሳናስቀድምህ ተሸንፈናል(፪)

የበረከት : ብቻ : ሆኗል : ስብከታችን

መስቀሉን : መሸከም : አይፈልግ : ስጋችን

መንፈስህን : ዘግተን : አስመርረነዋል

በምትናገረን : ጆሯችን : ተዘግቷል

አቤት መልሰን

መልሰን መልሰን

ከሄድንበት ርቀን(፪)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ