Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የወንጌል አደራ

Yewongel Adera

2012 · ትራክ 5 · 5:27 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለተቀበሉት : ለዚህ : አደራ

በእምነት : ቆሙ : እስከመጨረሻ

ሐዋርያቱ : ያለፉበት : ለወንጌሉ : ነው : የተሰዉት

በአሰቃቂ : ሞት : አለፈ : ሕይወታቸው

እልፍ : ምስክር : አይኑ : እያያቸው

ለአደራቸው : ነው : የጨከኑት : ላመኑበት

እየተበሉ : እየተሰቃዩ : የወንጌሉን : አደራ : ለእኛ : አቆዩ(x2)

ነገ : እንዳይነሳ : እግዚአብሔርን : የማያውቅ : ትውልድ

ማነው : ሕዝቡን : የሚመራው : ምሳሌ : እየሆነ

ወደ : አምላኩ : መንገድ (x2)

አለ : ምስክር : አለ : መሬቱ

ጻድቃን : ስለወንጌል : የተሰዉበት

በተራቡ : አንበሶች : እየተበሉ

የወንጌልን : አደራ : ለእኛ : አቆዩ

በሮም : ሜዳ : ላይ : ፈስሷል : ደማቸው

እልፍ : ምስክር : አይኑ : እያያቸው

ለአደራቸው : ነው : የጨከኑት : ለአመኑበት

እየተበሉ : እየተሰቃዩ : የወንጌልን : አደራ : ለእኛ : አቆዩ(x2)

ነገ : እንዳይነሳ : እግዚአብሔርን : የማያውቅ : ትውልድ

ማነው : ሕዝቡን : የሚመራው : ምሳሌ : እየሆነ

ወደ : አምላኩ : መንገድ

በአፄ : ዘረያዕቆብ : የተሰዉት

ለወንጌሉ : ነው : ጸንተው : የቆሙት

ከነነፍሳቸው : እየተቀበሩ : የወንጌልን : አደራ : ለእኛ : አቆዩ

በስደት : ዘመን : በአብዮቱ : ስያንገላቷቸው : በየእሥር : ቤቱ

ጨከኑ : ለእምነት : ለሃይማኖታቸው : ለተቀበሉት : ለአደራቸው

ነገ : እንዳይነሳ : እግዚአብሔርን : የማያውቅ : ትውልድ

ማነው : ሕዝቡን : የሚመራው : ምሳሌ : እየሆነ

ወደ : አምላኩ : መንገድ

እናንተ : ቅዱሳኖች : ያቆያችሁልኝ : የወንጌል : አደራ

እንዴት : ልሸከመው : እንዴት

እንዴት : ነው :?? : (እጅግ : ይከብዳልና)x2

የነገውን : ትውልድ : በእጄ : ላይ : ይኸውና

ዛሬ : ይውረድብኝ : እናንተን : የረዳው

የእግዚአብሔር : ፀጋ(x2)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ