Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መሃል ሰፋሪ

Mehal Sefari

2012 · ትራክ 7 · 6:16 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስር ሳይሰድድብኝ ህመሜ ሳይጠና

ከሕይወት ወጥቶ መሞት አለና

እምቢ ያለውን ልቤን ግራው

እዚህም እዚያም ይገድላል በለው (፪)

መልኬ እየተቀየረብኝ

ዛሬ አንተን ነገ ዓለምን ሆነብኝ

ወይ አልበረድኩኝ ወይ አልሞቅኩኝ

እንዲያው መሃል ላይ ሆኛለሁኝ

መሃል ሰፋሪ ሆኛለሁኝ

መሃል ሰፋሪ ከአፍህ ይተፋል (፪)

አወይ ልቤ ተመለስ

ጌታ ይሻልሃል የሚወድህ (፪)

ከአፍህ መተፋት እጅግ ያስፈራል

ክፉ ልማዴን መጣል ይሻላል

እምቢ ያለውን ልቤን ግራው

እዚህም እዚያም ይገድላል በለው (፪)

መልኬ እየተቀየረብኝ

ዛሬ አንተን ነገ ዓለምን ሆነብኝ

ወይ አልበረድኩኝ ወይ አልሞቅኩኝ

እንዲያው መሃል ላይ ሆኛለሁኝ

መሃል ሰፋሪ ሆኛለሁኝ

መሃል ሰፋሪ ከአፍህ ይተፋል (፪)

አወይ ልቤ ተመለስ

ጌታ ይሻልሃል የሚወድህ (፪)

ልቤስ አንድ ነው ሁለት ይመኛል

እዚህም እዚያም ብሎ ያስቸግራል

እምቢ ያለውን ልቤን ግራው

እዚህም እዚያም/የግብጽ:ሽንኩርት ይገድላል በለው (፪)

መልኬ እየተቀየረብኝ

ዛሬ አንተን ነገ ዓለምን ሆነብኝ

ወይ አልበረድኩኝ ወይ አልሞቅኩኝ

እንዲያው መሃል ላይ ሆኛለሁኝ

መሃል ሰፋሪ ሆኛለሁኝ

መሃል ሰፋሪ ከአፍህ ይተፋል (፪)

አወይ ልቤ ተመለስ

ጌታ ይሻልሃል የሚወድህ (፪)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ