ዘመኑ ሲከፋ
Zemenu Sikefa
2012 · ትራክ 3 · 5:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አየነው : በዓይናችን : ሲንከራተት : ሰው
መንፈስህ : ርቆት : ግራ : ሲገባው
ለካስ : አእምሮዬ : የተጠበቀው
የገዛ : መሻቴን : ስላልሰጠህኸኝ : ነው
አይ : ሰው : ያላንተ : እንዴት : ደካማ : ነው
አዝማች · Chorus
ክፉ : እና : ደጉንም : ጨርሶ : የማይለየው (x2)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዘመኑ : ሲከፋ : ጌታ : ፊቱን : ሲያዞር
የሰው : ልጅ : እንደ : እንሰሳ : ጉድ : ሲሆን
አቤት : ክፉንማ : ጆሮአችን : ለመደው
የማለዳ : ወሬ ቀኑማ ክፉ ነው
የምንሰማው ነገር ቀኑማ ክፉ ነው
ነውሩ ??? ሆነ ማይከለከለው
የኃጥያት ባንዲራ ሁሉም በእጁ ነው
የነውር ባንዲራ ሁሉም በደጁ ነው
ያልተሰማን ሰማ ያልታየውን አየ
አቤት ዘመኑም ይከፋል አቤት ሁሉም ይለወጣል
በዚህ ክፉ ዘመን ኧረ ማን ያወጣል
አቤት ጌታ ከአንተ በቀር አቤት ሰው ወዴት ይሸሻል
ቁጥር 3 · Verse 3
ለካስ : አእምሮዬ : የተጠበቀው
የገዛ : መሻቴን : ስላልሰጠኸኝ : ነው
አይ : ሰው : ያላንተ : እንዴት : ደካማ : ነው
አዝማች · Chorus
ክፉ : እና : ደጉንም : ጨርሶ : የማይለየው (፪x)
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር የማውቀው
የእኔ አምላክ ዛሬም ቅዱስ ነው
አንድ : ነገር : የማውቀው :
የእኔ : አምላክ : ዛሬም : ጻድቅ : ነው
ክፉ : ብንሰማም : ፅድቅ : የሌለ : ቢመስልም
አንድ : ነገር : የማውቀው :
የእኔ : አምላክ : ዛሬም : ቅዱስ : ነው
አንድ : ነገር : የማውቀው :
የእኔ : አምላክ : ዛሬም : ንጹህ : ነው
አንድ : ነገር : የማውቀው :
የእኔ : አምላክ : ዛሬም : ፃድቅ : ነው
ክፉ : ብንሰማም : ፅድቅ : የሌለ : ቢመስልም
አዝማች · Chorus
አንድ : ነገር : የማውቀው
የእኔ : አምላክ : ዛሬም : ቅዱስ : ነው
አንድ : ነገር : የማውቀው
የእኔ : አምላክ : ዛሬም : ንፁህ : ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ