ነፍሴ ሆይ አትዘናጊ
Nefsie Hoy Atezanagi
አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ነቀፋ ቢበዛ
አጃቢ ቢታጣ
ያልተጠባበቅነው መከራ ቢመጣ
ዕርፉን ጥለን አንዴ
ወደ ሌላም ሩጫ
የእግዚአብሔር ሥም ብቻ
ይሁነን ማምለጫ
ይህን ቀን ነፍሴ ሆይ!
አ ት ዘ ና ጊ !
ቃልኪዳንሽን ይዘሽ
በእግዚአብሔር ፊት ትጊ!
አዝማች · Chorus
<አዝ ፤ >
ነፍሴ ሆይ!
ኢየሱስን ስንቀበል
ከዚያም ደግሞ ለማገልገል
ክብር ዝናው ሳይጀመር
ከእግዚአብሔር ጋር የተባባልነው ምን ነበር?
ቁጥር 2 · Verse 2
ነፍሴ ሆይ!
ኢየሱስን ስንቀበል
ከዚያም ደግሞ ለማገልገል
አንቱ መባል ሳይጀመር
ከእግዚአብሔር ጋር የተባባልነው ምን ነበር?
ቁጥር 3 · Verse 3
፪) ዝና ቢበዛልን ፤ ስማችን ቢወጣ
ዕልፍ ገዳይ ተብሎ ዘፈንም ቢመጣ
ሰማይ ላንቀይር ማንም ላይ ሳንኮራ
በትዕግሥት እንፈጽም የእግዚአብሔርን ሥራ
አንዴም ነፍሴ ሆይ! አትዘናጊ!
ለቃል ኪዳንሽ በእግዚአብሔር ፊት ትጊ!
አዝማች · Chorus
<አዝ ፤ >
ነፍሴ ሆይ!
ኢየሱስን ስንቀበል
ከዚያም ደግሞ ለማገልገል
ክብር ዝናው ሳይጀመር
ከእግዚአብሔር ጋር የተባባልነው ምን ነበር?
ቁጥር 4 · Verse 4
ከተማ መግባት ሳይመጣ
ከእግዚአብሔር ጋር የተባባልነው ምን ነበር?
ቁጥር 5 · Verse 5
፫) መውጊያው ይነሣልን ብለን ስንለምነው
ብሎ የሚመልስልን ፀጋዬ በቂ ነው
እኛም እንደጳውሎስ እንኑር በጽናት
የእግዚአብሔርን መንግሥት በግብር ልንወርሳት
ግድየለም ነፍሴ ሆይ ! አትዘግዪ
ለቃልኪዳንሽ በእግዚአብሔር ፊት ትጊ!
አዝማች · Chorus
<አዝ ፤ >
ነፍሴ ሆይ!
ኢየሱስን ስንቀበል
ከዚያም ደግሞ ለማገልገል
ክብር ዝናው ሳይጀመር
ከእግዚአብሔር ጋር የተባባልነው ምን ነበር?
ቁጥር 6 · Verse 6
፬) ዕውነትን በውሸት የሚቀላቅሉ
ነጩን ካድ አድርገው ጥቁር ነው የሚሉ
ለጥቅም ያደሩ ወገኖች ቢነሡ
እኛ በታማኝነት እንኑር ለንጉሡ
አይደለም እንዴ ነፍሴ ሆይ! አትዘናጊ!
በፊርማችን በእግዚአብሔር ፊት ትጊ!
አዝማች · Chorus
<አዝ ፤ >
ነፍሴ ሆይ!
ኢየሱስን ስንቀበል
ከዚያም ደግሞ ለማገልገል
ክብር ዝናው ሳይጀመር
ከእግዚአብሔር ጋር የተባባልነው ምን ነበር?
ቁጥር 7 · Verse 7
አገር መዞር ሳይጀመር
ጓዳ እያለን የተባባልነው ምን ነበር?
ከእግዚአብሔር ጋር የተገባባነው ቃልኪዳን ይከበር!
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ