ጨመረው
Chemerew
ትራክ 3 · 7:44 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሻለቃ ሃምሣ አለቃ
ከፍ ዝቅ ቢያደርጉትም
ግድ የለውም ዳዊት
አይሞቀው አይበርደውም
የንጉሥ ልጅ ለማግባት
አያገለግልም (፪X)
አዝማች · Chorus
ከተማና ገጠር
ጸባይ አይቀይረው
ብቻ እግዚአብሔር ይክበር
ዳዊት ደስ ይለዋል
ያ መንፈስ በእኔም ላይ
ዘርን ቆጥሮ መጥቷል {፪X}
ከዘር ነው
የእግዚአብሔርን ክብር አናስነካም
ያልነው ከዘር ነው
ከዘር ነው (፪X)
ቁጥር 2 · Verse 2
እንጀራ ሲጠፋ
ቃልን በልተን ያደርነው
ከዘር ነው
እስቲ ቁጠሩት ዘሩን !
የአቋራጩን ክብር
አሻፈረኝ ያልነው
ከዘር ነው
እስቲ በሉ ከዘር ነው
ከእግዚአብሔር ተወልደን
ከዘር ነው
የዓመጽ ግብዣ ላይ
ጊዜ የለንም ያልነው
ከዘር ነው
ጨመረው ጨመረው
ዲያብሎስ ውጊያውን ጨመረው
ውጊያው ስለበዛ የማልቀደስ መሰለው
ጨመርኩኝ ጨመርኩኝ ጨመርኩኝ
ባሰብኝ ቅድስና
ካቻምናም በዛ ምሥጋና
ምሥጋና ፣ ምሥጋና
የሠዋሁት ለእግዚአብሔር ምሥጋና
ጠራው ከእግዚአብሔር ፊት
የበቀልን ደመና {፪X}
ቁጥር 3 · Verse 3
እዚህ ቢቆለፍ
እዚያ ቢዘጋ
ይገኝልኛል ኑሮ ቢናጋ
ብሎ ዲያብሎስ ቢወድቅ ቢነሣ
ከከፍታዬ ነቅነቅ አልልም
ከዚህ ከፍታ በቃ አልወርድም
አልወርድም ለሰይጣን ግብዣ
አልወርድም በምንም ዓይነት
አልወርድም ለሰይጣን ሃሣብ
አልወርድም በምንም ዓይነት
በሰይጣን ላይ እሣት ይውረድበት
አልወርድም ለሰይጣን ግብዣ
አልወርድም ወደ ርኩሰት
አልወርድም ኑሮን ፈርቼ
አልወርድም በምንም ዓይነት
በሰይጣን ላይ እሣት ይውረድበት
ቁጥር 4 · Verse 4
ሃሌሉያ!
አንዳንዶች በዓመጽ በልጽገው
ቢኖሩ እጅግ ተቀማጥለው
ለእግዚአብሔር ኖሬለት ብደኸይ
እግዚአብሔር ከእኔ ጋር የለም ወይ?
በቁሳቁስ ብዛት ክብሬ አይመዘንም
ሰይጣን በመንደሬ መድረክ አያገኝም {፪X}
ቁጥር 5 · Verse 5
አልሰማም የሰይጣንን ስብከት
ጉድለቴን እያየ ቢያወራ
በኃጢአት አንጣላ እንጂ
ቢያደርግ ባያደርገው ቢሠራ ባይሠራ
ለማንም አልምልም አልደራደርም
የሠራዊት አምላክ አለ ከእኔ ጋራ
አልሰማም የሰይጣንን ስብከት
ዙሪያዬ ን እያየ ቢያወራ
በኃጢአት አንጣላ እንጂ
ቢያደርግ ባያደርገው ቢሠራ ባይሠራ
ለማንም አልምልም አልደራደርም
የሠራዊት አምላክ አለ ከእኔ ጋራ
ጨመረው ጨመረው
ዲያብሎስ ውጊያውን ጨመረው
ውጊያው ስለበዛ የማልቀደስ መሰለው
ጨመርኩኝ ጨመርኩኝ ጨመርኩኝ
ባሰብኝ ቅድስና
ካቻምናም በዛ ምሥጋና
ምሥጋና ፣ ምሥጋና
የሠዋሁት ለእግዚአብሔር ምሥጋና
ጠራው ከእግዚአብሔር ፊት
የበቀልን ደመና {፪X}
ቁጥር 6 · Verse 6
አልያዝም! ዛሬም
ድል የእኔ ነው
ነገም ፣ ዓርበኛ ነኝ
ዛሬም የእግዚአብሔር ነኝ
ነገም በኢየሱስ ያልመጣው
አዲስ ሰይጣን የለም
ምንም አልሆንም
ዛሬም ሰላሜ ከኢየሱስ ነው
ነገም ድል የእኔ ነው
ዛሬም አልያዝም
ነገም በኢየሱስ ያልመጣው
አዲስ ሰይጣን የለም
አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን
ጫፉን እንዳትነካው
ብሎታል ጠላቴን
አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን
ይዘምራል ሽሸው ብሎታል ጠላቴን
አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን
ጫፉን እንዳትነካው ብሎታል ጠላቴን!
ሃሌሉያ !
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ