Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ታለፈ ያ ዘመን

Talefe Ya Zemen

2007 · ትራክ 1 · 7:50 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንዴት አልፈዋለሁ ያልኩትን ያንን ቀን

ክንድህ አሻገረኝ አለፍኩት ያንን ቀን

ዛሬስ ተረዳሁኝ ቆምኩኝ እንደገና

ቀና አልኩኝ ከአንገቴ ታለፈ ያ ዘመን

ታለፈ ያ ዘመን (፬x)

(በኢየሱስ የማይታለፍ ምን አለ)

ታለፈ ያ ዘመን (፬x)

ምንም ሳልናገር ቃል ሳይወጣ ከአፌ

ሁሉን መለሰና ሆነልኝ ድጋፌ

ያ ሁሉ ጥያቄ ኧረ ወዴት ገባ

ማንስ አበሰልኝ የዓይኖቼን እንባ

እንደ እናትም ሆነ ከእናትም በላይ

ብዙ አድርጐልኛል ኢየሱስ ኤልሻዳይ

እንደ አባትም ሆነ ከአባትም በላይ

ብዙ አድርጐልኛል ኢየሱስ ኤልሻዳይ (፪x)

መግለጥ አቅቶኝ ፍቅርህን በቋንቋ

ብዘምር ብዘምር ብሎኛል አሎወጣ

እስኪ ልሞክር ለመግለጽ ስለ አንተ

ደግሜ ልበልህ አንተ እኮ ፍቅር ነህ

አንተ እኮ ፍቅር ነህ (፮x)

አንተ እኮ ደግ ነህ (፮x)

አንተ እኮ ሩሩህ ነህ (፮x)

እንዴት አልፈዋለሁ ያልኩትን ያንን ቀን

ክንድህ አሻገረኝ አለፍኩት ያንን ቀን

ዛሬስ ተረዳሁኝ ቆምኩኝ እንደገና

ቀና አልኩኝ ከአንገቴ ታለፈ ያ ዘመን

ታለፈ ያ ዘመን (፫x)

ታለፈ ያ ዘመን (በኢየሱስ የማይታለፍ ምን አለ)

ታለፈ ያ ዘመን (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ