ውለታው አለብኝ
Wuletaw Alebegn
2007 · ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በጠላቴ መንደር በድል ላራመደኝ ኦሆ ላራመደኝ (፪x)
እኔስ የዚህ ጌታ ውለታው አለብኝ ኦሆ አለብኝ (፪x)
በክብር ላይ ክብር ክብርን ላለበሰኝ ኦሆ ላስታጠቀኝ (፪x)
ምነው ከዚህ በላይ እኔስ በሆንኩለት ኦሆ በሆንኩለት (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ዘመኑ የድል ነው የመከናዎን
ከአምላኬ የሰማሁት በመንፈስ ያወኩት የተረዳሁት
ዘመኑ የድል ነው የመከናዎን
ዘመኑ የድል ነው የመከናዎን (፪x)
አዝማች · Chorus
በጠራራ ጸሐይ ደመናም ሳይታይ ኦሆ ደመናም ሳይታይ (፪x)
ምንጭን አፈለቀ ጌታ ከዓለቱ ላይ ኦሆ ጌታ ከዓለቱ ላይ (፪x)
እኔ ምስክር ነኝ ከዓለቱ ጠጥቼ ኦሆ ከዓለቱ ጠጥቼ (፪x)
ዘመኑ የድል ነው እላለሁኝ ዛሬ ኦሆ እላለሁኝ ዛሬ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተረጋጋሁ መንፈሱ ሲነካኝ ተረጋጋሁ
ተረጋጋሁ ቅባቱ ሲነካኝ ተረጋጋሁ
አመለጥኩኝ ወዳጄን ሰምቼው አመለጥኩኝ
አመለጥኩኝ ጌታዬን ሰምቼው አመለጥኩኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ