ተደስቻለሁ
Tedeschalehu
2015 · ትራክ 2 · 8:58 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ነፍስም አልቀረልኝም (8)
ወደድኩህ ስትለኝ
ነፍስም አልቀረልኝም
ልጄ ነህ ስትለኝ
ነፍስም አልቀረልኝም
ጸድቀሃል ስትለኝ
ነፍስም አልቀረልኝም
ተርፈሃል ስትለኝ
ነፍስም አልቀረልኝም
ተደስቻለሁ እኔ ተደስቻለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ባደራረግህ ኢየሱሴ ተደስቻለሁ
ተደስቻለሁ በቃ ተደስቻለሁ
ሰበብ ፈልጌ ፈላልጌ አመልክሃለሁ
ተገርሜአለሁ እኔ ተገርሜአለሁ
ባደራረግህ የኔ ወዳጅ ተገርሜአለሁ
ተደንቄአለሁ በቃ ተደንቄአለሁ
ሰበብ ፈልጌ ፈላልጌ አመልክሃለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
አዋፋት ሲያዜሙ
ተራሮች ሲዘሉ
ወንዙ ሲያመልክህ
ባህር ሲታዘዙ
አየሁ አየሁና ዙሪያዬን ቃኝቼ
ሳጣ የማየውን አማትሬ አይቼ
እኔም በ ተራዬ
ደሞ የ ድርሻዬን
ልወጣ አልኩና
ያዝኩ በገናዬን
የ ምስጋና ነዶ (2)
ሊያቀርብልህ መጣ
ልቤ አንተን ወዶ (2)
አዝማች · Chorus
ተደስቻለሁ እኔ ተደስቻለሁ
ባደራረግህ ኢየሱሴ ተደስቻለሁ
ተደስቻለሁ በቃ ተደስቻለሁ
ሰበብ ፈልጌ ፈላልጌ አመልክሃለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
ተደስቻለሁ እኔስ ተደስቻለሁ
ባደራረግህ የኔ ኢየሱስ ተደስቻለሁ
ተገርሜአለሁ በቃ ተገርሜአለሁ
ሰበብ ፈልጌ ፈላልጌ አመልክሃለሁ
ቁጥር 5 · Verse 5
ቃል ሲወጣ ካፍህ ወደድኩህ (ወደድኩህ)
ትኩረቴን ቀልቤን ገዛው ፈለኩህ
በ አምልኮ በ ምስጋና ማደሪያህን
አጥናለሁ በ እጣን ከርቤ ዙፋንህን
አዝማች · Chorus
ተደስቻለሁ እኔ ተደስቻለሁ
ባደራረግህ ኢየሱሴ ተደስቻለሁ
ተደስቻለሁ በቃ ተደስቻለሁ
ሰበብ ፈልጌ ፈላልጌ አመልክሃለሁ
ቁጥር 6 · Verse 6
ተገርሜአለሁ እኔ ተገርሜአለሁ
ባደራረግህ የኔ ወዳጅ ተገርሜአለሁ
ተደንቄአለሁ በቃ ተደንቄአለሁ
ሰበብ ፈልጌ ፈላልጌ አመልክሃለሁ
ቁጥር 7 · Verse 7
ነፍሴ ደስ የሚላት
ነፍሴ የምታርፈው
በ ምስጋና በ አምልኮ ስትውል ነው (2)
አላውቅም ሌላ ደስታ ከዚህ ውጪ
ለኔ በቃ አልፈልግም ሌላ አማራጪ
በ ህልውና መገኘቱ ውስጥ መኖሬ
የ ኑሮዬ ልምምድ ነው መዘመሬ
አጥንቴም ስሜቴም ጅማቴም
ነፍሴ እና ቁርጭምጭሚቶቼም
ባንድላይ ለ ክብርህ ይዋሉ
ለተሰሩበት አላማ ሳይጎሉ
አዝማች · Chorus
ተደስቻለሁ እኔ ተደስቻለሁ
ባደራረግህ ኢየሱሴ ተደስቻለሁ
ተደስቻለሁ በቃ ተደስቻለሁ
ሰበብ ፈልጌ ፈላልጌ አመልክሃለሁ
ቁጥር 8 · Verse 8
ተገርሜአለሁ እኔ ተገርሜአለሁ
ባደራረግህ የኔ ወዳጅ ተገርሜአለሁ
ተደንቄአለሁ በቃ ተደንቄአለሁ
ሰበብ ፈልጌ ፈላልጌ አመልክሃለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ