ወዶ ዘማች
Wedo Zemach
2015 · ትራክ 3 · 4:44 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከተሸሸኩበት መንደሬ
መጣ ኢየሱስ ገባ ሰፈሬ
ጠራኝ ቀርቦ በቁልምጫው
ሊያስገባኝ ወደ ጉያው
የወዳጄ የአምላኬ
ጥሪው ደርሶኛል
ምን አደርጋለሁ
ቀሪው ዘመኔን ሰጥቼዋለሁ
ይስራበት ይክበርበት
ያለው አላማ ፈቃድ ሀሳቡ
ይጠቅለል በእኔ ይድረስ ከግቡ
አዝማች · Chorus
ሲጠራኝ (ክብር አይቶልኝ)
ሲለየኝ (ክብር አይቶልኝ)
ሲቀባኝ (ክብር አይቶልኝ)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሲመርጠኝ (ክብር አይቶልኝ) (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መገለጫው ነው መገለጫው
ለሰማይ ወኪል የምድር ጨው
የምድርን ክፋት
መርገም ሰባሪ
የሰላም ዘማች ለሰማይ ጥሪ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሲጠራኝ (ክብር አይቶልኝ)
ሲለየኝ (ክብር አይቶልኝ)
ሲቀባኝ (ክብር አይቶልኝ)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሲመርጠኝ (ክብር አይቶልኝ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ማያንገራግረው ማያመቻምቸው
ትዳር ባለበት ሰፈር
ራሱን የማይጠምደው
ጠሪውን ሲያስደስተው
ሲገኝ በጸና እምነቱ
ማረጉ ነው በላዩ
ሚታየው ሽልማቱ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ወዶ ዘማች ወዶ ዘማች
ለወንጌሉ ወዶ ዘማች
ፈቅዶ ዘማች ፈቅዶ ዘማች
ለዚህ ጥሪ ፈቅዶ ዘማች
ማነው (ወዶ ዘማች)
ማነው (ለዚህ ጥሪ)
ማነው (ራሱን ሰቶ)
ማነው (ጌታውን አስጠሪ)
ማነው (እኔ ነኝ)
ማነው (እኔ ነኝ)
ማነው (እኔ ነኛ)
ማነው (ለወንጌሉ)
ማነው (ዘማች አርበኛ)
ማነው (፬x)
ማነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ