አልረሳውም
Alresawem
2015 · ትራክ 4 · 5:54 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያደረክልኝን ውለታ
በምንም በምንም አልረሳም
ከየት እንዳነሳኸኝ
በምንም በምንም አልረሳም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከትላንቱ ለሊት ካስፈሪው
ከዚያ ከጨለማ
ነጥቀህ ስታወጣኝ ኢየሱስ
ማነው በዓይኑ ያላየ
ማነው ጆሮው ያልሰማ
ቁሻሻዬን ሸክሜን አራግፈህ
ሰው ስታደርገኝ
ያደረክልኝን ውለታ
በምንም በምንም አልረሳም (፭x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መነሻ እንደሌለው መድረሻዬ ላይ ቆሜ
የምሥጋና ቃሌን ለማጠፍ የረዳኝን ወዲያ ብዬ
ከእናቴ ማህጸን ስወጣ በስኬት ካባ ተሽሜ
ይህ ይመስል አልነካኝ ነፋሱ የማለፊያው የችግሬ
እኔም እንዳልሆነ አላወራም ቆሜ
ማን ረድቶኝ ማን አግዞኝ አልልም (፫x)
ጉልበቴ አመጣልኝ አልልም (፫x)
ጥበቤ በዝቶ እውቀቴ አልልም (፫x)
ያከማቸሁት ይህ ሃብቴ አልልም (፫x)
አላስብም እንደበረታሁ
አላስብም ከእግዚአብሄር/ከፀጋው ውጪ
አላስብም በጉብዝናዬ
አላስብም አለፍኩት ብዬ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከልጅነቴ እስከ እውቀቴ
ያሳደከኝ ያስተማርከኝ (፪x)
በፍቅር እጅህ አጉርሰኸኛል
መምህሬ ነህ መች ይረሳኛል (፪x)
ውጪውን አላየውም ላፍታ
አልደሰት በግብዝ ትዝታ
ገብቶኛል በቤቴ ያረከው
አብዝተህ ለእኔ ያትረፈረፍከው (፪x)
በእጄ ያለው ወርቅ አይሁንብኝ (፪x)
አላቀለውም አይወድቅብኝም (፪x)
በአንተ ጉያ ነው ዘላለሜ (፪x)
ስምህ ሆንዋል የኑሮ አለሜ (፪x)
አዝማች · Chorus
ና ና ና ና ና ና (4)
ውለታህ (አልረሳም)
ጥበቃህን (አልረሳም)
ምህረትን (አልረሳም)
እኔ አልረሳም (አልረሳም)
ምህረትን (አልረሳም)
ፍቅርህን (አልረሳም)
ያረከውን (አልረሳም)
ከቶ አልረሳም (አልረሳም)
አልረሳም
ውለታህን (አልረሳም)
ጥበቃህን (አልረሳም)
ፍቅርህን (አልረሳም)
እኔ አልረሳም (አልረሳም)
አሃ እኔ አልረሳም (አልረሳም)
ዎዎው (አልረሳም)
ኢየሱሴ (አልረሳም)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ