የአንተ ፍቅር ግን
Yante Feqer Gen
1996 · ትራክ 7 · 5:51 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ
መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ
የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ
ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ
እየሱሴ ለአንተ እጅ ሰጥቻለሁ
ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ብዙ የከበሩ በምድር ላይ ሞልተው
ታላቅ ነኝ ባዩን ልታሳፍረው
እኔን መረጥከኝ ዓሣ አጥማጁን ሰው
ኧረ ልዩ ነው ኢየሱሴ ፍቅርህ
ሀብታም: ደሀ አይል አመራረጥህ
ለእኔም ደረሰኝ ድንቅ ማዳንህ
አዝማች · Chorus
ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ
መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ
የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ
ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ
እየሱሴ ለአንተ እጅ ሰጥቻለሁ
ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
መች: ያልቃል ጥረቴ ለዚህ ሥጋዬ
ቀን ከሌት ስደክም መረቤን ጥዬ
ምንም ላላገኝ በድካም ዝዬ
አንተ ግን መጥተህ ተዓምርን ሰራህ
መላው ሕይወቴን መገረም ሞላ
ሥሜን ተግባሬን ኑሮዬን ቀየርክ
አዝማች · Chorus
ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ
መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ
የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ
ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ
እየሱሴ ለአንተ እጅ ሰጥቻለሁ
ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከኋላዬ ና ወድጄሃልሁ
ለማዳን ሥራ መርጬሃልሁ
ሰዎችን አጥማጅ አደርግሃልሁ
ኣለኝ ጌታዬ እኔም ተረታሁ
ከልብ ወደድኩህ ሕይወቴን ሰጠሁ
እስከ ዘለዓለም አመልክሃለሁ
አዝማች · Chorus
ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ
መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ
የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ
ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ
እየሱሴ ለአንተ እጅ ሰጥቻለሁ
ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
የዋህነትህ ትህትናህ ነው: የሳበኝ
በኃይል በጉልበት አላስገደድከኝ
ድንቅ ፍቅርህ ነው ያንበረከከኝ
ልከተል ወሰንኩ ከልብ ጌታዬ
በነገር ሁሉ አንተን ታምኜ
መረብ ታንኳዬን ሁሉንም ጥዬ
አዝማች · Chorus
ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ
መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ
የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ
ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ
እየሱሴ ለአንተ እጅ ሰጥቻለሁ
ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ