Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መስማማት

Mesmamat

1996 · ትራክ 5 · 6:06 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሀሳቤ የልቤ ባይሞላ

ያቀድኩት ነገር ባይሰካ

ላመስግን ልተው ማማረሬን

ያልከው ይሁን ጌታ

ያ መልካም ነው ለእኔ

ከአንተ ጋር መስማማት ይሻላል

መማረር ማኩረፍ ምን ያዋጣል

ፈቃድህ ይሁን ማለት መልካም

በጊዜው ነገር ውብ ይሆናል (፪x)

ችግሬ ረሃቤ ቢፀናም

ቁስሌ ባይደርቅ ፈውሴ ቢዘገይ

ከፈቀድከው ይሁን ማለት

አስተምረኝ ጌታዬ ትግስትን

ከአንተ ጋር መስማማት ይሻላል

መማረር ማኩረፍ ምን ያዋጣል

ፈቃድህ ይሁን ማለት መልካም

በጊዜው ነገር ውብ ይሆናል (፪x)

ጌታ ነህ ብትገል ብታድንም

መከራከር ከአንተ ጋር ኣይበጅም

ክፉ አይደለህም ጨካኝ

ለአላማህ : ነው ጌታ: የምትመራኝ

ከአንተ ጋር መስማማት ይሻላል

መማረር ማኩረፍ ምን ያዋጣል

ፈቃድህ ይሁን ማለት መልካም

በጊዜው ነገር ውብ ይሆናል (፪x)

አንተ ያልከው ይሻለኛል

የእራሴማ መቼ ያዋጣኛል

ትርፉ መመረር መቁሰል ነው

ለአንተ ሀሳብ :ጌታ መገዛት ጥሩ ነው

ከአንተ ጋር መስማማት ይሻላል

መማረር ማኩረፍ ምን ያዋጣል

ፈቃድህ ይሁን ማለት መልካም

በጊዜው ነገር ውብ ይሆናል (፪x)

በሥራህ ሁልጊዜ ጻድቅ ነህ

ተሳስተህስ መቼ ታውቃለህ

ሀሳቤን በሀሳብህ ጠቅልለው

ምኞቴንም ኢየሱስ እንደ ቃልህ አርገው

ከአንተ ጋር መስማማት ይሻላል

መማረር ማኩረፍ ምን ያዋጣል

ፈቃድህ ይሁን ማለት መልካም

በጊዜው ነገር ውብ ይሆናል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ