አንበሳ
Anbesa
1996 · ትራክ 1 · 6:51 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንበሳ የይሁዳ አንበሳ ነው
ንጉሥ ነው የጌቶችም ጌታ ነው
ሁሉንም አሸንፏል በክብር ከፍ ብሏል
ኧረ ማነው የሚመስለው
የእኛ ጌታ ልዩ ነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የታረደው በግ ኢየሱስ ጌታ ነው
ምሥጋናም ክብርም የተገባው ነው
ጥበብም ውዳሴም ለእርሱ ነው
ድል አድራጊ ጌታ ነው
አዝማች · Chorus
አንበሳ የይሁዳ አንበሳ ነው
ንጉሥ ነው የጌቶችም ጌታ ነው
ሁሉንም አሸንፏል በክብር ከፍ ብሏል
ኧረ ማነው የሚመስለው
የእኛ ጌታ ልዩ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች
ወድቀው በፊቱ የሚሰግዱለት
ዘለዓለም ሊነግሥ ይገባዋል
ኢየሱስ ሁሉን ረቷል
አዝማች · Chorus
አንበሳ የይሁዳ አንበሳ ነው
ንጉሥ ነው የጌቶችም ጌታ ነው
ሁሉንም አሸንፏል በክብር ከፍ ብሏል
ኧረ ማነው የሚመስለው
የእኛ ጌታ ልዩ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በአምባ ላይ ፈረስ የተቀመጠው
እውነተኛና ታማኝ የሆነው
በትክክል ይፈርዳል ይዋጋል
ጌታን ማን ይችለዋል?!
አዝማች · Chorus
አንበሳ የይሁዳ አንበሳ ነው
ንጉሥ ነው የጌቶችም ጌታ ነው
ሁሉንም አሸንፏል በክብር ከፍ ብሏል
ኧረ ማነው የሚመስለው
የእኛ ጌታ ልዩ ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከእርሱ ሌላ ማንም አያውቀው
ከሥሞች በላይ ታላቅ ሥም አለው
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው
የነገሥታት ንጉሥ ነው
አዝማች · Chorus
አንበሳ የይሁዳ አንበሳ ነው
ንጉሥ ነው የጌቶችም ጌታ ነው
ሁሉንም አሸንፏል በክብር ከፍ ብሏል
ኧረ ማነው የሚመስለው
የእኛ ጌታ ልዩ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ