ኦ ተመስገን
Oh Temesgen
1996 · ትራክ 4 · 6:01 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኦ ተመሥገን (፪x)
ስላደረክልኝ ድንቅ ነገር
ስላደረክልኝ መልካም ነገር
ምስኪኑን ረዳኸኝ ከትቢያ አነሳኸኝ
አልችልም እኔስ ልገልፀው ውለታህ በዛብኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የምህረት ዓይኖችህ ይከታተሉኛል
የበደሌን ብዛት ጌታ ፍቅርህ ሸፍኖታል
ሀዘንም ሲያጠቃኝ ከጐኔ ቆመሃል
መፅናናቴ ነህ ኢየሱስ አበርትተኸኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
ኦ ተመሥገን (፪x)
ስላደረክልኝ ድንቅ ነገር
ስላደረክልኝ መልካም ነገር
ምስኪኑን ረዳኸኝ ከትቢያ አነሳኸኝ
አልችልም እኔስ ልገልፀው ውለታህ በዛብኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታዬ ተባረክ ሁሉም በአንተ ሆነ
አንድ ሁለት ብዬ የማወራው የለም ከእኔ የሆነ
እውነት ነፍሴን ላፍስስ ሥምህን ልወድሰው
የመዝሙሬ ዜማ ቅኔ ማደሪያህን ይሙላው (፪x)
አዝማች · Chorus
ኦ ተመሥገን (፪x)
ስላደረክልኝ ድንቅ ነገር
ስላደረክልኝ መልካም ነገር
ምስኪኑን ረዳኸኝ ከትቢያ አነሳኸኝ
አልችልም እኔስ ልገልፀው ውለታህ በዛብኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በሰው የተናቀ የተጣለውን ሰው
መደነቂያ እንዲሆን ጌታ ለክብርህ አቆምከው
ብርታት ትሆናለህ ሞገስ ትሆናለህ
ኧረ እንዳንተ ማነው ጌታ/ኢየሱስ ሁሉን ትችላለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኦ ተመሥገን (፪x)
ስላደረክልኝ ድንቅ ነገር
ስላደረክልኝ መልካም ነገር
ምስኪኑን ረዳኸኝ ከትቢያ አነሳኸኝ
አልችልም እኔስ ልገልፀው ውለታህ በዛብኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አስደናቂው ፍቅርህ ከሳበኝ ጀምሮ
ያደረክልኝ ውለታ አያልቅም ተቆጥሮ
ጌታ የአንተ ሥራ በምን ቋንቋ ልግለፅ
ማለት የምችለው ይኸን ነው ኢየሱስ/ውድዬ ተባረክ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኦ ተመሥገን (፪x)
ስላደረክልኝ ድንቅ ነገር
ስላደረክልኝ መልካም ነገር
ምስኪኑን ረዳኸኝ ከትቢያ አነሳኸኝ
አልችልም እኔስ ልገልፀው ውለታህ በዛብኝ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ