Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የሕይወቴ ሚስጥር

Yehiwotie Mister

1996 · ትራክ 8 · 6:26 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የሕይወት ሚስጥር ሳይገባቸው ሲከተሉ ለእንጀራቸው

አልተስማሙም ከአንተ ጋራ ተመለሱ ወደ ኋላ

እኔስ በርቶልኛል መዳን ሆኖልኛል

ሕይወት አንተ ብቻ ኢየሱስ የለህ አቻ

ምንም ላላገኝ ከአንተ ርቄ ላይሆንልኝ

ጥሜ ላይረካ የዓለም ኑሮ ላይፈይደኝ

ከአንተ ወዴት እሄዳለሁኝ ኢየሱስ እንደ አንተ

ለእኔ የሚሆን መቼም ቢሆን አላየሁኝ (፪x)

መድኃኒቴ አንተ ልዩ ነህ ማንም የለም የሚመስልህ

ኢየሱስ ለእኔ መከታዬ ጋሻዬ ነህ ከለላዬ

ከአንተ አልለይም ሌላው አይሆንልኝም

የሕይወት ቃል አለህ ጥሜን ታረካለህ

ምንም ላላገኝ ከአንተ ርቄ ላይሆንልኝ

ጥሜ ላይረካ የዓለም ኑሮ ላይፈይደኝ

ከአንተ ወዴት እሄዳለሁኝ ኢየሱስ እንደ አንተ

ለእኔ የሚሆን መቼም ቢሆን አላየሁኝ (፪x)

ከአንተ ጋር ኑሮ ተመችቶኛል ኢየሱሴ ጉያህ : ሞቆኛል

በፍቅርህ ነው እኔን የሳብከኝ እስከሞት ድረስ የወደድከኝ

በቃ ወስኛለሁ አንተን መርጫለሁ

እርስቴ ነህ ብያለሁ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ

ምንም ላላገኝ ከአንተ ርቄ ላይሆንልኝ

ጥሜ ላይረካ የዓለም ኑሮ ላይፈይደኝ

ከአንተ ወዴት እሄዳለሁኝ ኢየሱስ እንደ አንተ

ለእኔ የሚሆን መቼም ቢሆን አላየሁኝ (፪x)

ኢየሱስ ሕይወቴን አብርተሃል እኔነቴን ለውጠሃል

አልለይህም ወድሃለሁ ከአንተ ውጪ ጨለማ ነው

ግዛኝ የእኔ ጌታ ልስገድ ጠዋት ማታ

ነፍሴን የተቤዠህ አንተው ትሻሃለኛለህ

ምንም ላላገኝ ከአንተ ርቄ ላይሆንልኝ

ጥሜ ላይረካ የዓለም ኑሮ ላይፈይደኝ

ከአንተ ወዴት እሄዳለሁኝ ኢየሱስ እንደ አንተ

ለእኔ የሚሆን መቼም ቢሆን አላየሁኝ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ