ያረፈበት ዓይኔ
Yarefebet Aynie
2005 · ትራክ 5 · 4:29 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንዲህ የምሆነው በዚህ ጉብዝናዬ
ያረፈበት ዓይኔ የወደደው ልቤ
በኢየሱስ ቁንጅና ላይ ነው ያለው ሀሳቤ
ያረፈበት ዓይኔ የወደደው ቀልቤ
በኢየሱስ ቁንጅና ላይ ነው ያለው ሃሳቤ
አዝማች · Chorus
ፍጥረት በሙሉ ይየው ይየው ጌታን ይየው
አንዴ ቀምሶ ካጣጣመው ሌላ አያሰኘው
ሌላውን ላልወድ ሌላዉን ላልሻ
በሌላ ላልታለል ሌላዉን ላልሻ
ተማርኬያለሁ እስከመጨረሻ (፪x)
አመልከዋለሁ እስከመጨረሻ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ያገር ቆንጆ ነኝ ባዩ ከውዴ ሲተያዩ
ያመረ መሳይ ዉበቱ ዉዴ ይበልጠዋል በስንቱ
ያገር ቆንጆ ነኝ ባዩ ከየሱስ ሲተያዩ
ያመረ መሳይ ዉበት ዉዴ በዛበት በስንቱ
ፍጥረት በሙሉ ይየዉ ይየው ጌታን ይየዉ
አንዴ ቀምሶ ካጣጣመዉ ሌላ አያሰኘዉ
አዝማች · Chorus
እንዲህ የምሆነው (፪x)
የኢየሱስ ውበቱ ከሁሉ በልጦብኝ ነው
በዚህ ጉብዝናዬ ለዓለም ማልገዛው
ያዘጋጀው ክብር ከዓለም በልጦብኝ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አገር ሁሉ ያደነቀው ሰዓሊው የሳለው
አይ ሞኙ መች ገባው የኔን ቆንጆን አላየው
አገር ሁሉ ያደነቀው ሰዓሊው የሳለው
አይ ሞኙ መች ገባው ኢየሱሴን አላየው
ፍጥረት በሙሉ ይየዉ ይየው ጌታን ይየዉ
አንዴ ቀምሶ ካጣጣመዉ ሌላ አያሰኘዉ
አዝማች · Chorus
ውበትን ላልፈልግ ዓለምን ላልሻ
በዓለም ላልታለል ውበትን ላልሻ
አግኘቸዋለሁ እስከመጨረሻ (፪x)
ወርሼዋለሁ እስከመጨረሻ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እንዲህ የምሆነው (፪x)
የኢየሱስ ውበቱ ከሁሉ በልጦብኝ ነው
በዚህ ጉብዝናዬ ለዓለም ማልገዛው
ያዘጋጀው ክብር ከዓለም በልጦብኝ ነው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ