Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዛሬማ ዓይኔ ያየው

Zariema Aynie Yayew

2005 · ትራክ 1 · 5:27 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዛሬማ ዓይኔ ያየው በለጠ ጆሮዬ ከሰማው

በላዬ ስለ ሾምኩህ ልቤን ኩራት አለው (፪x)

ንግሥናህን ሳስበው ውስጤ ተደንቀ መገረም ተሞላ

አንድ ነህ ለሕይወቴ አላውቅም ከአንተ ሌላ

የለኝም ከአንተ ሌላ

እንዴት ያምራል እንዴት ውብ ነው

ንጉሥ ወግህ ስርዓትህ ሆ

ኧረ እንዴት ያምራል እንዴት ውብ ነው

አገዛዝህ ቅን ነው ፍርድህ (፪x)

ልዩ ነህ አንተ አትጠገብም (፬x)

ልዩ ነህ አንተ አትጠገብም

ልዩ ነህ አንተ አልጠገብኩህም (፪x)

ማለዳም ማለዳ አዲስነትህ ነው ልዩ ያደረገህ

ዕድሜውን ከአንተ ጋራ ፈጅቶ

የትኛው ሰው ለመደህ የትኛው ሰው ጠገበህ

ከትላንትናው ዛሬ ከዛሬው ነገ ይለያል የክብርህ ነፀብራቁ

ስለዚህ በልጠህብኛል ከአልማዝ ከወርቅ ከዕንቁ (፪x)

ጆሮዬ ድምጽን ሰምቶ አይጠግብም

ዓይኔ ክብርህን አይቶ አይጠግብም

ምላሴ ጽድቅህን አውርቶ አይጠግብም

ቃላቴ አደናንቆህ አይጠግብም

ልዩ ነህ አንተ አትጠገብም (፬x)

ልዩ ነህ አንተ አትጠገብም

ልዩ ነህ አንተ አልጠገብኩህም (፪x)

እንዴት ያምራል እንዴት ውብ ነው

ንጉሥ ወግህ ስርዓትህ ሆ

ኧረ አንዴት ያምራል እንዴት ውብ ነው

አገዛዝህ ቅን ነው ፍርድህ (፪x)

ተወዳዳሪ አቻ እና እኩያ

የለህም ልዩ ነህ ለዘላለም (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ