ከጉባዔው መሃል
Kegubaew Mehal
2005 · ትራክ 2 · 6:41 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከጉባዔው መሃል ብዙ ሕዝብም ካለበት
ተጋባዥ ሰው ሆኜ ያኔ በፍርሃት
ህዝቡ ብዙ ግን ባንድ ድምፅ አቤት ዝማርያቸው
መፅሐፍ ተከፍቶ ይነገራል ሰምቼ ማላውቀው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከቃሉ የህይወት ውሃ ወደልቤ ፈሰሰ
ሳላቅማማ ጠጣሁት ውስጤም ረሰረስ
ኧረ እንዴት ያለ ቀን ነው ዳግመኛ ተወለድኩኝ
በልቤ አምኝ በአፌም መሰከርኩኝ
በዚያን ቀን አሃሃ ታሪኬ ተቀየረ
በዚያን ቀን ኦሆሆ ቀንበሬ ተሰበረ
በዚያን ቀን ሽክሜም ቀለለልኝ
በዚያን ቀን ኢየሱስ ጌታ ነው አልኩኝ
አዝማች · Chorus
እንዳንተ ያለ ጌታ
አንተን መሳይ ወዳጅ
እንዳንተ ያለ መሃሪ
አንተን መሳይ አምላክ
ለማወቅ ተከፈቱ ዓይኖቼ
የመዳንን ቃል ሰምቼ
ወስኜ አንተን ያገኘሁባት
ያችን ቀን አልረሳት
ያችን ቀን ልባርካት (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ውዴ ደጁን ሲያንኳኳ በሬን ከፈትኩለት
ከእኔ ጋር እራት በላ የዋህ ነው በልቡ ትሁት
ተቆረሰ የሕይወት እንጀራ ዓይኖቼም ተከፈቱ
እንደንቦሳ ዘለልኩኝ አይረሳኝም ዕለቱ
በዚያን ቀን አሃሃ ኃጢያቴ ተሰረየ
በዚያን ቀን ኦሆሆ በሰማይ ደስታ ሆነ
በዚያን ቀን በአብ ቀኝ ተቀመጥኩኝ
በዚያን ቀን አምላክን እኔ ወረስኩኝ
አዝማች · Chorus
እንዳንተ ያለ ጌታ
አንተን መሳይ ወዳጅ
እንዳንተ ያለ መሃሪ
አንተን መሳይ አምላክ
ለማወቅ ተከፈቱ ዓይኖቼ
የመዳንን ቃል ሰምቼ
ወስኜ አንተን ያገኘሁባት
ያችን ቀን አልረሳት
ያችን ቀን ልባርካት (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ይገርማል እኔን መውደድህ ይገርማል
ይገርማል እኔን ማሰብህ ይገርማል (፪x)
ይገርማል እኔን መውደድህ
ይገርማል እኔን ማሰብህ
ይገርማል እኔን ማፍቀርህ ይገርማል (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ