Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሥምህን ስጠራ

Semehen Setera

2005 · ትራክ 3 · 4:33 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሥምህን ስጠራ በከንፈሮቼ

ደጋግመው ይለኛል መላው እኔነቴ

እስቲ ልደጋግመው ኢየሱሴ ብዬ

በረከቴ እኮ ነው ለነፍሴ ተድላዬ

ስደጋግመውማ (፪x)

ኑሮዬ ይባረካል ሰላሜ ይበዛልኛል

ኑሮዬ ይባረካል ደስታዬ ይበዛልኛል

እወድሃለሁ ስልህ ከልቤ እንደሆነ

አንተው ታውቀዋለህ (፪x)

እራስህ ታውቀዋለህ (፪x)

እከተላለው ስልህ ወስኜ እንደሆነ

ልቤን ታውቀዋለህ (፪x)

ውስጤንም ታውቀዋለህ (፪x)

የማይጠገብ ጣዕም የማያልቅ መዓዛዉ

ፍጥረት ተደነቀ ጌታዬን ስጠራዉ

እኔም አላረፍኩ አበዛሁ መጥራትን

ኢየሱስ ጌታ ነው ኦሆ አዳኝ ነው ማለት

ስደጋግመውማ (፪x)

ደረቁ ይለመልማል አበባው ፍሬን ይሰጣል

ደረቁ ይለመልማል ቡቃያው ይሰጣል

እወድሃለሁ ስልህ ከልቤ እንደሆነ

አንተው ታውቀዋለህ (፪x)

እራስህ ታውቀዋለህ (፪x)

እከተላለው ስልህ ወስኜ እንደሆነ

ልቤን ታውቀዋለህ (፪x)

ውስጤንም ታውቀዋለህ (፪x)

በጠዋት በማታ ስሙን ሳነሳሳው

ለእኔ ድል ሆነኝ ለጠላት አበሳ

ኢየሱስ ስልበት ጠላት ተሸበረ

መንግስቱ ፈረሰ ወጥመድ ተሰበረ

ስደጋግመውማ (፪x)

ጠላቴ ይዋረዳል ሽንፈቱን ይከናንባል

ጠላቴ ይዋረዳል ምርኮዬን ይመልሰዋል

እወድሃለሁ ስልህ ከልቤ እንደሆነ

አንተው ታውቀዋለህ (፪x)

እራስህ ታውቀዋለህ (፪x)

እከተላለው ስልህ ወስኜ እንደሆነ

ልቤን ታውቀዋለህ (፪x)

ውስጤንም ታውቀዋለህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ