በጥበብህ በችሎታህ
Betebebih Bechelotah
2005 · ትራክ 6 · 5:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በጥበብህ በችሎታህ እንዳንተ ያለ ማነው ጌታ (፪x)
ዕውቀትህ የተለየ ፍጥረት እንዳንተ አልሰማ አላየ (፪x)
(አሃሃ) ትልቅ ነህ ብልህም
(አሃሃ) ከዚያም ትልቃለህ
(አሃሃ) ጌታዬ እግዚአብሔር
(አሃሃ) በማን ልመስልህ
አዝማች · Chorus
ከምልህ በላይ ነህ የኔ ጌታ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰው ከፍታ መጨረሻ መርገጫህ ነው ላንተ መነሻ (፪x)
ታች ብወርድ ላይ ቢወጣ የሚመስልህ አንድም ታጣ
ታች ብወርድ ላይ ቢወጣ የሚያህልህ አንድም ታጣ
(አሃሃ) ከህዝብህ ጋር ሆኜ
(አሃሃ) ስምህን ባውድስ
(አሃሃ) እንኳን ልጨርሰው
(አሃሃ) ከመሃሉም እልደርስ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጥበብህ ብዙ ነው የኔ ጌታ (፪x)
ዕውቀትህ ሠፊ ነው የኔ ጌታ (፪x)
ገዢዎችን ትሾማለህ ሲያሻህ ደግሞ ታወርዳለህ
ገዢዎችን ትሾማለህ ሲያሻህ ደግሞ ትሽራለህ
ልዕልናህ እጅግ ከፍ ያለ ካንተ በላይ ማንም የለ (፪x)
(አሃሃ) ከህዝብህ ጋር ሆኜ
(አሃሃ) ስምህን ባውድስ
(አሃሃ) እንኳን ልጨርሰው
(አሃሃ) ከመሃሉም እልደርስ
አዝማች · Chorus
ከምልህ በላይ ነህ የኔ ጌታ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ልገልፅህ አልችልም የኔ ጌታ (፪x)
ላምልክ እንደገና አሃ (፫x)
አምላኬ ነህና
ላንግሥ እንደገና አሃ (፫x)
ንጉሤ ነህና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ