ይቅርታ
Yeqerta
ትራክ 2 · 3:58 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"ማሜ አሁን እኮ ያለሽ እድል
አባትሽህን ሄዶ ይቅርታ መጠየቅ ነው
አዎ አውቃለሁ እንዴ ግን እኔ ይቅርታ እጠይቀዋለሁ?
እንዴ ለምንድን ነው ሄደሽ ይቅርታ ማትጠይቄው?
መጽሃፍ ቅዱስ እኮ ስለይቅርታ
በጣም ብዙ ነገር ነው የሚያስተምረን
አዎ አውቃለሁ ብዙ ነገር ነው የሚያስተምረን
ግን እኮ አንዳንዴ አውቄ አጠፋለሁ
አንዳንዴ ደግሞ ሳላውቅ አጠፋለሁ
እየተሳሳትኩኝ እኮ ነው የተሸገርኩት
አይ ልክ አይደለሽም
አሁን ቀስ ብለሽ ሂጂና ይቅርታ መጠየቅ አለብሽ
እንደተቀመጠ ቀስ ብለሽ ወደ እርሱ ሄደሽ ይቅርታ ጠይቂ
ወይኔ ጉዴ እፈራለሁ እኮ
እንዳይገርፈኝ ብዬ እኮ ፈርቼ ነው
አትፍሪ አይዞሽ ሂጂ ሂጂ አይዞሽ አትፍሪ "
ቁጥር 2 · Verse 2
ስለተሳሳትኩኝ ስላጠፋሁት
አውቄም ሳላውቁም ሁሉ ላረኩት
ጥፈተኝነቴ ገብቶኝ ይኸው ወጥቻለሁና
አዝማች · Chorus
ድጋሜ አላጠፋም ለዛሬም ይቅርታ (፪x)
ይቅርታ (፪x) ይቅርታ (፬x)
ይቅርታ (፪x) ይቅርታ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ያጠፋሸው ጥፋት በሙሉ ገብቶሻል
ቶሎ ብለሽ መጥተሽ ይቅርታ ብለሻል
ድጋሚ አታጥፌ እንጂ ልጄ
እኔም በጣም እወድሻለሁ
ነይ ልሳምሽ አንዴ ይቅር ብዬሻለሁ
አዝማች · Chorus
I love you (እወድሻለሁ) (፮x)
I love you (እወድሻለሁ) (፮x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ