ልጄ ሆይ ቃሌን ጠብቅ
Lejie Hoy Qalien Tebeq
ትራክ 1 · 2:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"ሚጡ ሚጡ ነይና አባባ እንቅልፋቸው ሳይመጣ
ምከሩን እንበላቸው እንደትላንትና
ውይ እኔ እኮ በጣም ነው ምወደው የሳቸውን ምክር
እሺ ነይ ደስ ይለኛል
አባባ አባባ? ምክር ምከሩን አባባ
ምክር አላችሁ? አዎ አዎ
እሺ እስቲ ዛሬ እስኪ ደግሞ ከምሳሌ መጽሃፍ
እስቲ አንድ ምክር ልምከራቹህ አሺ እሺ
እንደዚህ ይላል ልጆቼ
አዝማች · Chorus
ልጄ ሆይ ቃሌን ጠብቅ
ትዕዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ
ትዕዛዜንም ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ ያላል
የእግዚአብሔርን ቃል ስትጠብቁ በሕይወት ትኖራላችሁ እሺ?
እሺ! ጐበዝ ልጆች
እስቲ እቼን መዝሙር ደስ እያላችሁ ዘምሯት
እሺ አባባ ሚጡ ነይ!
ጥበብ ማስተዋል ስጠኝ እያላችሁ አምላክን ለምኑት "
ቁጥር 2 · Verse 2
ልጄ ሆይ ቃሌን ጠብቅ
ትዕዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ
ትዕዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ
ህጌንም እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቅ
በጣቶችህ ተሰራቸው በልብህ ጽላትም ጻፋቸው
ጥበብን አንቺ እህቴ ነሽ በላት
ማስተዋልንም ወዳጄ ብለህ ጥራት
ልጄ ሆይ ቃሌን ጠብቂ
ትዕዛዜንም በአንቺ ዘንድ ሸሽጊ
ትዕዛዜን ጠብቂ በሕይወትም ትኖሪያለሽ
ህጌንም እንደ ዐይንሽ ብሌን ጠብቂ
በጣቶችሽ ተሰራያቸው በልብሽ ጽላትም ጻፊያቸው
ጥበብን አንቺ እህቴ ነሽ በያት
ማስተዋልንም ወዳጄ ብለሽ ጥራያት
አዝማች · Chorus
ጥበብ ማስተዋል ዕውቀትን ስጠኝ
ጌታ ጥበብ ማስተዋል ዕውቀትን ስጠኝ (ለእኔ)
ጥበብ ማስተዋል ዕውቀትን ስጠኝ
ጌታ ጥበብ ማስተዋል ዕውቀትን ስጠኝ (ለእኔ)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ